37 entries.
Hana Sishu
from
Aldie, VA
wrote on November 3, 2023
at
2:38 am
There are a multitude of adjectives in the English dictionary, many of which describe Belisha perfectly. However, when I think about her one word comes to mind: nurturing. Belisha was the kind of person who never spoke ill of others and was genuinely kind to everyone she met. But, for me, Belisha’s defining quality was her selfless love.
When I first met Belisha I was 5 years old. We lived with Belisha and Abe until my parents and I finally got a place of our own. I didn’t know either of them and I was scared and missed my dad when we first came to Virginia. The first night with Abe and Belisha was fun. My mom, Belea, and I slept on the bed and Abe, like a gentleman, volunteered to sleep on the couch in their tiny one bedroom apartment in Alexandria. My mom fell asleep quickly but Belisha stayed up with me talking, laughing, and playing etemite until I eventually got tired and fell asleep. From the first day she met me Belisha treated me like a daughter….her daughter. As I got older she became a friend, my best friend in fact. She would always listen to my rants about unimportant things like whatever new artist I was listening to, or my favorite book and why she should read it, and my tangents about how amazing—or awful—new music for our next band concert was. However, she wasn’t only my best friend, she was—in her words not mine—“everyone’s bestie.”
Her love and affection was pure. Her purest form of love was reserved for her children. Betty, Amy, Melat. Your mother was an incredible woman, someone everyone deserved to know, she was not only a good person but a good Christian, and you should be very proud of that. She was cherished by so many people and you are not alone in your grief. Abe, you and Belea both hold a special place in my heart; I hope to have a relationship and a love like you and Belisha shared someday. Belisha is in a much better place now, and although that doesn’t lessen the pain, I am hopeful that one day we all reach a point where we can share our happy memories of her and smile instead of cry.
Freh
wrote on November 3, 2023
at
2:00 am
Over 15 years ago, I had the pleasure of meeting Belisha for the first time through Abisha who was and still is a good friend of my family. She was a delightful and beautiful young lady, and all my family enjoyed having her, even on that initial encounter. Both of us eventually relocated to the United States, maintaining a close connection and making an effort to visit each other whenever possible.
One unforgettable memory happened when Belisha and her family visited us for our son's christening. At that moment, she was expecting their second child, Amy, while their eldest, Bethy, was merely one year old. Despite all the reasons they had not to come, they embarked on a seven-hour overnight drive to attend the service. This act of unwavering commitment exemplified Belisha's character – she would go to great lengths to stand by your side when you needed her.
Less than a year later, my family reciprocated by visiting them in Virginia for a two-night stay. When it was time for us to leave for another family commitment, Belisha, true to her nature, begged us to extend our stay. Regrettably, we declined her kind offer, leaving for our next destination. We could sense her disappointment as we departed.
Tragically, the unexpected occurred – we never reached our intended destination. Our eight-month-old baby fell seriously ill, prompting us to rush him to the emergency room. His condition worsened, leading to his transfer to the INOVA Fairfax Children's Hospital in an ambulance, a terrifying experience for my husband and I. We spent the night and the following day at the hospital, and we couldn't help but regret our decision to leave Belisha's home early. It became a valuable lesson – Belisha's desire for us to stay was rooted in genuine love, a lesson we would carry with us.
In the last five years, we lost touch with a belief that we will continue from where we left of when we meet next, which I deeply regret to this day. We only learned of her illness belatedly, and even then, I refused to accept the possibility of losing her. I didn't call her, didn't visit, not even once. Even in her final moments, I clung to the belief that it shall all be passing, a story to tell. It was a form of self-denial that now fills me with overwhelming remorse. No amount of retrospective actions can change the fact that I never visited her, and I must live with that regret. However, I pray that I could always stay close to her family, and be there for them whenever they need someone.
Belishaye, I hope you can find it in your heart to forgive me for not visiting you during your illness. Rest in peace, my beautiful and kind friend.
Until we meet again!
Afomeya(Pomi)
from
Dublin,Ohio
wrote on November 2, 2023
at
10:16 pm
No words can describe how I am feeling, Belisha. I always wonder why someone like you would be taken from us. But then I think of what your response would be "Whatever happens, it is God's plan Pomiye." Firstly, I thank god for giving me such a blessed, strong, smart, and faithful godmother. Your humility made you believe you didn't do enough for me, but Belisha you did more than any Krista Enat would ever do. It was like there was no age difference between us because we could talk for hours and hours, laughing and telling each other the ups and downs of life like two best friends. I always felt like I had a shoulder to cry on when you were here. You would constantly beg to come and see me during my health struggles in life. You would never forget to say I love you before you end any conversation. You would without a miss say" Pomiye est men legzalesh, men lelakelsh". If only I knew of the suffering you were enduring.
But that suffering, you made sure no one saw it in you. I will never forget our last conversation, Belishaye. I cried at the thought of you being critically ill and you told me from that hospital bed
"Pomiye, I am feeling very well thanks to god. After this time passes, I will visit you every chance I get." If only I knew you would leave us very soon. I will always regret not seeing you before you passed, not talking to you every moment I got, and not coming to Virginia more often, but Belishaye you were right, it was God's plan. He wanted you in the place you belong.
This world is simply not good enough for a person like you. There is a big gaping hole when I think about you not being here but you have left a forever lasting mark in my heart. I will always remember and cherish the beautiful moments we had. Goodbye is not forever. Goodbye is not the end. It simply means I'lI miss you until we meet again. May you rest in peace Belishaye.
I will always love and miss you
Your Goddaughter Afomeya Baye (Pomi)
Liya
from
silver spring
wrote on November 1, 2023
at
11:10 pm
በልሻ የተለየ የሚወደድ ስብዕና ያላት በጣም ተወዳጅ፣ ሰው የምትወድ እህታችን ነበረች። ከሁሉ የሚገርመው ለዚህኛው በአል ቤቷ ከሄድን የሚቀጥለውንም እንድንመጣ ትጠይቀናለች። ከሁሉ የሚገርመኝ ግን ለሁለተኛ ጊዜ ታማ ልናያት ስንመጣ በወዳጅ ጓደኞቿ ተከባ ነበርና ለብቻዋ ላገኛት አልቻልኩም ። ስወጣ በልሻዬ ማታ ልደውልልሽና ላውራሽ አልኳት እሺ ብላኝ ወዲያው ጠራችኝና ከሷ ጋር ስለማወራው የራሴ ጉዳይ ጠየቀችኝ፣ በጣም ተገረምኩ ሰው እንደዛ ባለ ህመምና ስቃይ ውስጥ ሆኖ እንዴት ስለሰው ሊያስብ ይችላል? ምን አይነት ስብዕና ነው? በህመሟ ስንጨነቅ ውለን ሄደን ስናያት ቀሎን እንመለሳለን። አፅናንታ አሳስቃ ትመልሰናለች። በልሻዬ ነብስሽን ከቅዱሳን ጋር ያሳርፍልን።
በልሻዬ የፍቅር የወዳጅነት የለጋስነትና የእንግዳ ተቀባይነት እንዲሁም የእናትነት ተምሳሌት ነበረች ሰው በልቶ የሚጠግብ የማይምስላት ደግ ; ፈገግታዋ ሁሌ ከፊቷ የማይጠፋ የእኛም የሳቃችን ምንጭ ጨዋታ ከቁም ነገር ጋር የምትችልበት እህታችን ሰብሳቢያችን እና መሪያችን ነበረች
ከብዙ ትዝታዎቼ በቅርቡ የሆነውን ላስታውስ ጠዋት ጠዋት ወክ እናድርግ ብለን ከእህቶቼ ጋር በምንጏዝበት ጊዜ እሷም ልጆች ት/ቤት ስታደርስ ታየናለች እናም ምን እያደረጋችሁ ነው ?ብላ ስትጠይቀን ወክ እንደምናደርግ ነገርናት እሷም በመሳቅ እኔም አብሬያችሁ እሆናለሁ በማለት እንዴት ወክ እንደሚደረግ በማሳየት ጉዞአችንን ጀመርን እኛም ትንሽ እንደሄድን ላብ በላብ ሆንን እንዴ ቀስ በይ እንጂ በልሻዬ ስንላት እናንተ እኮ እንደቁራሌው ነው ሰፈር የምትዞሩት እንጂ ወክ አይባልም ብላ ያሳቀችንንም ያሳቀቀችንንም አልረሳውም ከዛም መልስ በቤቷ ቁርስ አዘጋጅታ በመጋበዝ ድካማችንን ታጠፋልን ነበር :: ስንቱን ልፃፈው በውስጤ ብዙ ነገር አለ ግን እግዚአብሔር እርሱ የወደደውን አደረገ ሁሌም ውስጣችን ነሽ እንወድሻለን በልሻዬ እኛም መጥተን እስከምናገኝሽ በሰላም እረፊልን
አምላከ ቅዱሳን እህታችንን ከደግጎቹ ጋር ይደምርልን
Selam
from
Addis Ababa
wrote on November 1, 2023
at
2:41 pm
She was such an amazing strong woman. She is like my first person to mention when it comes to about my future life, I have been dreaming to be like her since high school and still now, l always always talk about how gifted she is; that she has everything that everyone wants. I always wonder how could I become like her a strong, independent, spiritual ,generous, outgoing beautiful soul but things happen for a reason that I understand. And God wants us to realize something by taking you with him. God bless your pure heart belishaye rest in heaven!
Assefa Mideksa
from
Ambo, Ethiopia
wrote on November 1, 2023
at
7:45 am
ይኼ ጥያቄ ምንም እንኳን ከባድ ቢሆንም፤ ባጭሩ በልሻዬ ማለት ለሰው በጣም አሳቢ፣ ሰውን እንደ ችሎታው የምትቀርብ ወይም የሚትረዳ፣ ትንሽ ወይም ትልቅ ሳትል ሰውን የምትመክር፣ ውሸትን አጥብቃ የሚትጠላ፣ አንድ ሰው አንድን ነገር ችላለው ብሎ እራሱን ካሳመነ ምንም ነገር ማድረግ እንደ ሚችል የምትገፋፋ፣ ለትንሽ ለትልቁ ተቆርቋሪ፣ በተለይ ሰው ኑሮውን አሸንፎ ሲኖር ከባለቤቱ ባልተናነሰ ደስታን የሚሰጣት እህታች ነበረች።
Asamenech
from
Addis Ababa
wrote on November 1, 2023
at
7:25 am
የእኔና የበሌ ትዉወቅ መቀሌ ዩንቨርስቲ ነዉ በሌ መልካም ጓደኛዬ ነበረች በነበረን የ4ዓመት ቆይታችን ዲፓርትመንታችም ቢለያይ ብዙ ጊዜ ግን አብረን ነዉ የምናሳልፈዉ አብረን ነዉ ቤተክርስቲያን የምንሄደዉ፡፡ በሌ አሁን ላለኝ ሂወት ትልቅ አስተዋፆ ያደረገችልን ጓደኛዬ እህቴም ናት በዛ ወቀት እኔን ወደ መንፈሳዊ ቦታ ባተመራኝ ማን ያዉቃል…የምናገለግለዉም በጎአድራጎት ላይ ስለነበር መስጠት ምን እንደሆነ አሳዉቃኛለች፡፡ ተመርቀን እንደወጣን እኔ ወደ ክፍለሀገር ስራ አግኝቼ ልሄድ ስል ተገናኘንና ለመሄድ መወሰኔን ስነግራት ጥሩ ነዉ ትንሽ ሰርተሸ ነይ ግን እዛ ስትኖሪ መንፈሳዊ ሂወትሽን አደራ በተቻለሽ መጠን የምትከራይዉ ቤት ከቤተክርስቲያን እንዳይርቅ ምክንያቱም ሰንፈሽ ትጠፊያለሽ አትሄጂም ቤትሽ ከስራሽ ቢርቅ ግዴታሽ ስለሆነ ወደ ስራ መሄድ ከዛ አትቀሪም አለችኝ በፍፁም የማረሳዉ ንግግር ነዉ፡፡ ከዛ በኃላ ሂወት ሩጫ ናት እሳም ወጣች ብዙም በአካል ተገናኝቶ ለማዉራት እዱሉን አላገኘሁም ግን አልፎ አልፎ በቴክስት እናወራ ነበር፡፡ በሌ መልካም ጥሩና ሩህሩህ ጓደኛዬ ነበረች እሳን ማጣት ለባል፤ ለልጅ፤ ለእናት በጣም ከባድ ነዉ ግን የሰራቻቸዉ መልካም ስራዎችን እያወሱ መኖር ግን ትልቅነት ነዉና አቤ በዚሁ ቀጥልበት ጠንካራ የልጆች አባት ሆነህ እሰትኖር እራይዋንም ስታስፈፅም የቤሌም ነፍስ በሰላም ታርፋለች
እህቴ፤ ጓደኛዬ፤ መካሪዬ በልሻዬ እ/ር ነፍስሽን በአፀደ ገነት ያኑርልን አሜን!
Daniel Negatu
from
Aldie
wrote on November 1, 2023
at
5:22 am
I have no words to express her kindness and compassion towards everyone she reminds me my mother and all Ethiopian kind mothers though i should have comfort her on her rainy days which I didn’t because of this American life that would be the credit which lives with me through my life but she is such a pure human being with full of kindness and love and grace i definitely know that her place is haven and she will be smiling upon us from there because that’s is where she belongs the kingdom of heaven. finally i say may you rest in peace Belesha and may God comfort You Abba and the whole family
Amen Abebe
from
Aldie, VA
wrote on October 31, 2023
at
7:35 pm
She would always call me ቁጭቁጭ because one day when I was still a baby it was her first time leaving me at home with my grandma to go to work and all I did was talk and talk and talk and I wouldn’t stop. So she started to call me ቁጭቁጭ. I still remember, two years ago she got really sick and told us she had cancer. She had two surgerys that year. After she got better around December or November 2022 she started to exercise a lot. Then, she stopped because they realized she had a lot of pain in her leg. Then, it started to get to her arm. She had several doctors appointments and they realized that her cancer was coming back. In May she went to the hospital for around a month. When she came back she was a bit better and stayed home for a while but after that she started going back and forth from the hospital. This month she went to the hospital very very sick. I still have the memory. I was sleeping on the floor with my dad because it was fasting season and in the middle of the night he got a call and they told him to rush to the hospital. I spent the rest of the day worrying if she passed away. It is much better than seeing her suffer and be in pain. Now we know she is happy and with God. Thank you.
Yodit Ayalew
from
Aldie
wrote on October 31, 2023
at
7:04 pm
I struggle to find the words to express the depth of sorrow and emptiness I feel. It seems like no words can truly capture the profound impact you had on my life and the magnitude of the grief that still lingers within me.
I have known you for almost two decades now. However, what has permanently moved me to my core is your constant love for your children. A specific conversation I had with you in your last days rings in my head every day. It is a testament to the kind of person you were—warm, loving, and devoted.
Watching your family's determination and resilience, I can only imagine that their faith and memories of you help them during the most trying times. And undoubtedly, if it weren't for God, such sorrow would have left all of us devastated!
Belshaye, your absence left a void no one would ever fill; however, it has taught me to cherish every relationship, moment, and fleeting opportunity life presents. Your presence in my life served as a reminder to cherish the present, to be in the moment, and to show unconditional love. Memories of our time together often flood my mind, and it's painful to know those moments won't come again. But amidst the pain, I'm grateful for having known you and for having shared laughter, tears, and countless unforgettable memories.
Although I miss you terribly, I appreciate and cherish our time together. Rest well, dear friend. Your memory will forever be eternal.
With endless love and sorrow,
Yodit
Haymanot
from
Addis Ababa
wrote on October 31, 2023
at
6:10 pm
እንዴት ነሽ የኔ እናት በልሻዬ እንሆ ከተለያየን ወራቶች አለፉ በአካል ብንለያይም በመንፈስ አሁንም ቅርባችን እንዳለሽ ሁሌም ይሰማኛል።
የኔ እናት ሁሌም እኔን ሀይሚ ልጄ ናት ትያለሽ አቤት እንደዛ ስትይ አቤት ደስታዬ ያንቺ ልጅ መባሉ ለኔ ትልቅ ክብር ነው ።
በልሻዬ የኔ እናት የልጅነት እድሜን ካንቺ ጋር በማሳለፌ አለም ላይ ካሉ እድለኞች አንደኛዋ ነኝ አቤት ፍቅርሽ አቤት እንክብካቤሽ አቤት ምክርሽ ሁሉ ነገርሽ ወደር አይገኝለትም ሁልጊዜም በልጅነቴ አጠገቤ ነበርሽ ፀጉሬን ሰርተሽ አስጠኝተሽኝ ሁሉን አርገሽልኝ አሳድገሽኛል።
በልሻዬ የኔ እናት አንቺ አለሽ ማለት ቤታችን ሙሉ ነው። የትምህርት ቤት ጎደኞችሽ የሰፈር ጐረቤት ሁሉም ቤታችን ይመጣሉ ሁሉንም የትምርት አይነት በተለይ ማትስ ትምርት በጣም ጕበዝ ስለነበርሽ ተራ በተራ እንድታስጠኛቸዉ ወረፋ ይይዛሉ ። ሁል ጊዜም ይገርመኛል ባንቺ ምክንያት ቤታችን በሳቅ በሰው ፍቅር የተሞላ ነበር።
ከዛም ዪኒቨርስቲ ስትገቢ ለኔ ትልቁ የሀዘን ቀን ነበር ምክንያቱም አንቺ የለሽማ ካጠገቤ አንድ ቀን እንኳን ባስ ካመለጠሽ ያለኝ ደስታ እንዴት እንደምናፍቅሽ እንደእንጀራ እንደውሃ ትርቢኝ ትጠሚኝ ነበር። ያ ጊዜ አስካሁን አይረሳኝም አንዳሁን መስሎ ይታየኛል።
በልሻዬ ወደ ውጪ ሀገር ሄደሽ ደሞ ሁሌ በስልክ የምናረጋቸው ንግግሮች ምክሮችሽ ሁሉ ነገሮች ከዉስጤ አይጠፍም። ሁሌም የተሻለ ቦታ እንድደርስ የማታረጊው ጥረት የለም የተለያዬ ስራዋች እንድሰራ ያላረግሽው ጥረት የለም በመጨርሻም ተሳክቶ እውን ሆንዋል።
በልሻዬ ሁሌም ለቤተሰቦችሽ ምታስቢ ምትጨነቂ ነበርሽ ሁሉም ሰው ቢማር ጕበዝ ቢሆን ተምሮም ቆንጆ ውጤት አምጥቶ ጠንክሮ ቢሰራ ትያለሽ ለትምርት ለጥናት ያለሽ አመለካከት ይገርመኛል የሚማር ሰው በጣም ትወጃለሽ ሰው ሲማር ሲያድግ ደስ ይልሻል።
በልሻዬ ካንቺ ብዙ ተምሬያለው ቀና መሆን የተቸገረን መርዳትን ለሰው ማሰብን ቤተሰብን መውደድን ሰው መውደድን ጥንካሬን ባለን ነገር አመስጋኝ መሆን ብርታትን አይበገሬነትን ትእግስትን ፅናትን ፍቅርን ዘርዝሬ ማልጨርሰው ብዙ ነገርን ካንቺ ተምሬያለው።
በልሻዬ አንቺ ማለት ልብሽ ቅን እጅግ በጣም ደግ የተቸገረን ማለፍ ማትችዬ
በልሻዬ አንቺ ማለት ለሰው በጎ ምታስቢ ሰው ሁሉ ከችግር እንዲወጣ በቻልሽ መጠን የምታግዢ ።
በልሻዬ አንቺ ማለት በጣም ቆንጆ ስትስቂ ቤቱ ሞቅ ምታረጊ ፈገግታሽ
የሚያምር ከላይም ከውስጥም ውብ የሆንሽ ነሽ።
በልሻዬ አንቺ ማለት ጨዋታ አዋቂ ከሁሉ ተግባቢ ቁም ነገረኛ ነበርሽ።
በልሻዬ አንቺ ማለት ህመምሽን ደብቀሽ የሰውን ችግር ምትፈቺ
በልሻዬ አንቺ ማለት ምንም ህመምሽን የማታሳይ በውስጥሽ የምትይዢ
በልሻዬ አንቺ ማለት ቤተሰብሽን የምትወጅ ሀሜትን የማታውቂ ንፁህ እናት ነበርሽ።
ለኛም በጥንካሬሽ በብርታትሽ በአይበገሬነትሽ ምንም ችግር ቢመጣ በፅናት ምታልፊውን ሁሌም ለኛ አርአያ ሆነሽ ስናስብሽ ስንዘክርሽ እንኖራለን።
በልዬ ያንቺን እረፍት ሳስበው ሁሌም ለምን ግን እላለሁ አምርሬ አለቅሳለሁ ተስፋ አጣለሁ ግን ደሞ ፈጣሪ ከኛ በላይ ወዶሻልና ብዬ አስባለሁ ደሞም እኛም ነገ ተረኛ እንደሆን ሳስብ አንቺስ መልካም ሰርተሽ ተወደሽ ተፈቅረሽ ወደ አምላክሽ ሄድሽ ወየው ለኛ እላለው።
በልሻዬ ላንቺ ትልቁም ትንሹም ያላዘነ ያላለቀስ ሰው የለም ይህም ምን ያህል በሰው ዘንድ የምትወደጂ በሰው ትልቅ ቦታ ያለሽ እናት ነሽ።
በልሻዬ በመጨረሻ ጊዜያቶች በስልክ ያወራናቸው ሁሉ ሁሌም በልቤ ውሰጥ ይኖራሉ።
ሁሌም የምትዬኝ ሀይሚ ጕበዝ ሁኚ ጠንካራ ሀኚ የምትይኝ ሁሌም በልቤ ይኖራል።
በመጨረሻም ለአብሻዬ ለቤትዬ ለኤምሻ ለሜላትዬ ለቦብሻዬ ለመላው ቤተሰብ መፅናናትን ይስጥልን።
በልሻዬ የኔ እናት የኔ ወርቅ የኔ ሁሉ ነገር የኔ ልዪ ሁሌም እወድሻለው አፈቅርሻለው።
በልሻዬ ነብስሽ በገነት ትረፍ
ያንቺው ሀይሚ
Hiwot
from
Aldie
wrote on October 31, 2023
at
3:09 pm
በልሻ ሳልጠግባት የተለየችኝ ውድ እህቴ ናት :: እኔም በህይወቴ እንደ እርሳ ቤተሰቡን የሚወድ ሰው የማውቅ አይመስለኝም::
ድንቅ እህቴ ጋር እስከዛሬ ያወራሁት ሁሉ በእያንዳንዳ እርምጃ ትዝ ይለኛል:: በጥቂቱ እንሆ::
ከእለታት በአንደኛው ቀን በምሰራበት የግሮሰሪ ስቶር እያለሁ ከፍተኛ የሆነ ስቶርም ይነሳል :: ቨርጂኒያ ላይ መብራት ይጠፋል በወደቁ ዛፎች ምክንያት መንገዶች ይዘጋሉ:: ጊዜው በጣም አስፈሪ ነበር:: ዝናቡም እላቆመም:: ስልክ ራሱ ለተወሰነ ጊዜ መስራት አቆመ:: የምደውልበት አልነበረኝም:: በልሻ ጋር ደወልኩ:: "አቤን ልላከው?" ነበር የመጀመሪያ ጥያቄዋ:: ቢምጣ በወደድሁ ግን አልተቀበልኳትም :: በኔ ህሊና መንገድ ላይ ችግር ቢገጥመውስ የምትሰስተው ሰው ብዬ እምቢ አልኳት:: በልዬ እህቴ እንዳልፈራ አበረታችኝ እና ወደእነርሱ ቤት እንዴትም ደረስኩ:: ለሶስት ቀን አብሬያት ከርሜ አስተናግዳኝ ሁኔታዎች ወደነበሩበት ሲመለሱ እኔም ወደቤቴ ተመለስኩ::
ሰው ሰው ሀገር መጥቶ መድረሻ በጠፉው ሰዓት ምን እንደሚሰማውታውቁት ይመስለኛል:: በልዬ ሰው አለኝ ብዬ በማላስብበት ጊዜ ቤተክርስቲያን አግኝታኝ ነገ እኔ ቢሮ እንድትመጪ ብላ እንደቀልድ ረዳት የሂሳብ ሰራተኛ አድርጋ አስቀጠረችኝ:: ስሜቱ ልዮ ነበር:: ኤሚዬን እርጉዝ ነበረች:: በጣም ልዮ ጊዜ አብረን አሳለፍን::
ከቤትዬ እርግዝና እስከ አሜን ብዙ ደስ የሚሉ ጊዜያትን አሳልፈናል:: ሳቁ የፊቱ ፈገግታ ለአንዲት ደቂቃ የማይለወጥ ሰው ያየሁት አርሷን ነው:: ፍቅር የአምላክ ስጦታ ብቻ ነው ሁሉም ሰው አይሰጠውም:: መስጠትም : እንግዳ መቀበልም ስጦታ ነው:: እርሳ የዚህ ስጦታ ባለቤት ናት:: ቤቷ ሄዶ ሳይጠግብ ሳይስቅ ደስ ሳይለው የሚመለስ አይኖርም:: የዛኔ ሁላችን ሳናገባ ሳንወልድ በነበረ ሰአት በልሻ ቤት ገብተን የፈለግነውን ሰርተን በልተን ጠጥተን ኖረናል:: የሚገርመው በሌም አቤም ሳይኖሩ ቤት ስትሄዱ ቁልፉን ካለበት አውጥተን ቤት ገብተን በልተን ጠጥተን ተኝተን እንወጣለን:: በፍፁም አትሳቀቁም:: አቤን አስነስቼ አበልሻ ጋር ያደርኩበትም ጊዜ አይረሳኝም::
የእናቶች ውይይት በነበረን ግዜ በጣም ልዮ የሆኑ ተሞክሮዎቿን አጋርታናለች:: ብዙ ተምሬባታለሁ :: በልዮ እንደምታጫውተን ሁሉ ለቁም ነገርም የሚደርስባት የለም::
ለሁል ግዜ የማልረሳት ውድ እህቴ የተወችው አሻራ ብዙ ነው:: የሚወራም የማይወራም ብዙ አለ:: በጊዜ ሩጫዋን የጨረሰች መልካም እህቴ በህይወቷም በሞቷም አስተማሪዮ ሆናለች:: ከእህቶች ጋር ስናወራ "በልዮ እንዲህብላ ነበር " የዘወትር ቃላችን ነው:: በህይወቴ ስላወቅኳቸው ከምደሰትባቸው ሰዎች አንዳ በልዮ ዘወትር እናስብሻለን:: እግዚአብሔር የወደደሽ እንደሆንሽ መአዛ ስራሽ ይመሰክራልና እንፅናናለን::
Yemarshet Gebreyohannes
from
Greer, SC
wrote on October 31, 2023
at
1:31 pm
በልሻዬ ማመን ይከብዳል መቼስ እየከበደንም ተቀበልነው እውነትም ሄደሻል። እሱ የፈቀደውን በፈቀደው ጊዜ ይወስዳል። እኛም መቼ እንደሆንን እና በምን እንደምንጠራ ስለማናውቅ ስለምንረሳው ግን እንደዚህ ከአጠገባችን ሰው ሲለየን ነው መሄድ የሚባል ነገር መኖሩንም የምናስተውለው። በየዕለቱ ልንጠራ እንደምንችል ብናስብ ኖሮ እንደዚህ ባልከበደን ነበር። እግዚአብሔር ከወዳጆቹ ከቅዱሳኑ ጋር ከእመብርሃን ጋር ልጄ ወዳጄ ብሎ እንደተቀበለሽ ምንም ጥርጥር የለኝም ለኛም በረከትሽ ይድረሰን። በልሻን የማውቃት ከአቤ ጋር ጓደኝነት ከጀመሩ ከቀናት በኋላ ጀምሮ ነው። በልሻ በጣም ደግ፣ ሳቂታ፣ ተጫዋች እንግዳ ተቀባይ፣ ከሁሉም አይነት ሰው ጋር ተግባቢ፣ የእግዚአብሔር ሰው ናት ወደ ቤቷ ነው የሄደችው። በነበረን ጊዜያት ሁሉ አንድም ቀን ቁም ነገር ሳናወራ እንደቀለድን ነው የተለያየነው። የህመሟን ነገር በትክክል ባለመስማቴ ማለፏን ለማመን በጣም ነበር የተቸገርኩት እስካሁንም ይከብደኛል። እግሯን እንዳመማት ነበር የሰማነው ሆስፒታል ስትገባ ጸልዩ ሲባልም ቢበዛ የፈራሁት ምናልባት ከከፋ እግሯን የሚያሳጣት ወይም እንደልብ መንቀሳቀስ ላትችል ነው የሚል ነበር እንጂ ምንም እዚህ የሚደርስ ህመም እንደነበራት አላወቅንም። እንደልምድ ሆኖ ሁሌም አቤ እና በልሻ ከግሩፓችን እኛን የጠይቃሉ እንጂ እነሱን እንዴት ናችሁ ብሉ እጥብቆ መጠየቅ አልተለመደም። ያው ቀልድና ጨዋያ ብቻም ስለሆነ ሃሳባችንም ወደዛ አይሄድልንም። ባለፉት ሁለት ዓመታት ከአቤ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች አውርተናል፣ ስለሌሎች ጓደኞቻችን እንዴት እንርዳቸው ብለን ሁሉ ያወራንበት ቀን ነበር፣ ለአገልግሎት ሌላ ስቴት እንዲሄድ ሳስገድደው ነበር በዚህ ሁሉ ጊዜ እኔም እጠንክሬ እናንተ እንዴት ናችሁ ብዬ አልጠየኩ እሱም ትንፍሽ አላለም። እንደተለመደው ያንን ሁሉ መከራ ተሸክመውም ለሌላ ሰው ይጨነቁ ስለነበር መገመት አይቻልም ነበር። እድለኛ ሆነን ከዓመት በፊት እቤታቸው ሄደን እግኝተናቸው ነበር። ለምን ያንን የመሰለ ጸጉር ቆረጥሽው ብዬ በልሻን ጠየኳት ባክሽ ኮቪድ ላይ እየተንጨባረረ ሲያስቸግረኝ ጎመድኩት አለችኝ በዛው እንደልማዷ ርእስ ቀየረች መሰለኝ ምንም ለመገመትም እድሉም አልነበረም። ሁሉንም ታሪክ የሰማሁት ካረፈች በኋላ ነበር። ይኼንን ሁሉ ስትታመም ባለመስማቴ፣ ሄጀ ባለማአየቴ፣ እይዞሽ ባለማለቴ ለብዙ ቀናት ከባድ ጥፋተኝነት፣ ራስ ወዳድነት ተሰምቶኛል። እግዜብሔር የወደደው ሆነ እንግዲህ ለዘላለም ዕረፍተ ነፍስ ያድልስግ ውድ እህቴ። ሁላችንም ወደዛው መሆናችንን ስለምንረሳ ከቅርባችን ሰው ሲወሰድ ይከብዳል። እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ቤተሰቦችሽን እጽናንቶ ይጠብቅልሽ። በዛ ሁሉ ሃዘን ውስጥ ኝ ብዙ የሚያጽናኑ የሚያስቀኑ እና በልሻን ለካ በደንብ አላውቃትም ያስባሉኝ ስራዎችሽን ሰምቻለሁ። ሰዎቹ ስለ በልሻ ሲናገሩ መስራት ያለባትን ሁሉ ሰርታ ሰለጨረሰች ይሆን የወሰዳት? ብዬ እያሰብኩ ነበር። የሽኝት መርሐ ግብሩ ላይ የተናገሩትን ሰዎች ሁሉ መስማት በጣም ያጽናና ነበር። ሁሉ ሰው ውስጥ የፍቅር፣ የእምነት፣ የእናትነት፣ የአገልጋይነት፣ የትጋትና ጥንካሬ፣ የእንግዳ ተቀባይነት፣ የተቸገሩ ያዘኑ የባዘኑ መጠጊያ፣ መጽናኛ የቤተሰብና የልጅ አያያዝ መልካም ምልክት አትማ ነው የሄደችው። እዛ መድረክ ላይ ከተነገሩት ሁሉ በጣም ልቤን የነኩኝ እና የተጽናናሁባቸውን ሁለት ነጥቦች ባነሳ፡
እንድ አባት ስለበልሻ ከገለጹ በኋላ በህመሟ ጊዜ አብረው ስለነበር እንዲህ አሉ “እግዚአብሔር ደጋግ ሰዎችን ከሰማዕታትም በረከት እንዲሳተፉ ጣዕሙን እንዲቀምሱ በመከራ ይፈትናቸዋል። የህመሟ ጽናት እሱን እስታወሰኝ” ብለው የገለጹበት አገላለጽ ይገርም ነበር።
ሁለተኛው አንዲት ልጅ እንዴት በልሻ የሁሉም ልጆች bestie እንደሆነች ገልጻ ያሳየቻት ምሳሌነት በሚገርም አባባል እንደዚህ በማለት ገልጻዋለች “I hope one day I will have a relationship and love like Abe and Belisha shared” ለታዳጌ ወጣቶቻችን በዚህ መልኩ መልካም ምሳሌ ሆኖ ማለፍ ትልቅ መታደል ነው።
ከዚህ በላይ ኝ የገረመኝ እዚሁ እቤቴ ልጄ ምን ሆነሽ ነው አለችኝ በልሻ አረፈች አሉኝ አልኳት who is Belisha? Bethi and Amy’s mom, noo…she was such a kind person, last summer was the first time she saw me but she made me feel home the moment I met her and when we left she asked Bethy and Amy to get me a present and I got one…. በልሻ ብዚ ጸጋ ያላት ልጅ ናጥ እግዚአብሔር ልጆቿን በጥበብ፣ በሞገስ ያሳድግላት፣ ለቁም ነገር ያብቃላቸው ይጠብቃቸው። መንፈስ ቅዱስ ባወቀ በውስጣቸው ጥንካሬውን ይስጣቸው። እንኳን እነሱን እኛንስ እየጠበቀን አይደል? አቤ ወንድሜ እግዚአብሔር ካንተ ጋር ይኑር፣ ያጽናህ! በልሻ ሁሌም እንወድሻለን።
Theodrows
from
Aldie
wrote on October 31, 2023
at
12:03 pm
በልሻ እንዴት እገልፃታለሁ ከአንድ ሚሊዮን አንድ በዚህ አለም ላይ ተከስተው ፤ ከፍ ብለው ደምቀው አይተናቸው ሳንጠግባቸው እንደሚያልፉ ተወርዋሪ ኮከብ ማለት ናት ። በግሌ ከበልሻዬ ጋር በሕይወቴ ዝቅታ እና ከፍታ መንገድ ላይ ተገናኝተናል ። ብዙ ሳንተዋወቅ “ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ የሚለውን” የጌታን ትዕዛዝ የፈጸመች ኋላም ቤተስብ ስንሆን ለወንድሞችህ የበለጠ አድርግ የሚለውን ትእዛዝ በእውነተኛ ፍቅር ወይንም አጋፔ ኖራ ያስተማረችኝ አህቴ እና ጎደኛዬ ነች ። በሕይወቷም በህልፈቷም የሕይወትን ሚስጥር አሰተምራኛለች ። ከእንግዲህ ምን እላለሁ ከማልቀስ በፊት እነኋ የሁሉ እንባ የሚታበስበት ፤ ለቅሶ እና ህማም ወደሌለበት ወደ ጌታዋ ደስታ ገብታለችና ወደ እርሷ ለመሄድ ዳግም በእውነተኛው አለም ላያት እናፍቃለሁ ።
Rahel
from
Aldie, VA
wrote on October 31, 2023
at
11:16 am
በልሻዬ ተወልዳ እስከ 5 አመቷ ድረስ አብረን ነበርን። በነዚያ 5 ዓመታት ከቤታችን ላሞች የሚታለብ ትኩስ ወተት እየጠጣች የእናቷንም ጡት እስከ 5 ዓመቷ ጠብታ አደገች። በጣም ድንቡሽቡሽ ስለነበረች እኔ ብቻ የምጠራት ስም ነበራት፤ ቹሉ ነበረ የምላት። ከ 5 ዓመቷ በኋላ ወደ አዲስ አበባ መጣች፤ ከዛ በኋላ አብሬአት የማደግ እድሉ ባይኖረኝም ክረምት ላይ ትመጣ ነበረ። ክረምት ስትመጣ እሷ አማርኛ ብቻ ስለምትናገር አባታችን ደግሞ ኦሮምኛ እና አማርኛ እየቀላቀለ ስለሚናገር ማታ ማታ ሁሌ ቤታችን በሳቅ የተሞላ ነበረ።
በልሻ ማለት ለኔ በእርግጥ የታናሼ ታናሽ ናት ግን ከልጅነቷ ጀምሮ በጣም ሳቂታ እና ተጫዋች ነበረች።
እንደ በልሹ ከቤታችን ወተት እና የእናታችንን ጡት የጠባ የለም። ወተት የምትጠጣው የመጀመሪያዋ ላም ስትታለብ ኩባያዋን ይዛ ትቆማለች፣ ልክ ሲያልቅ ትኩሱ ከነአረፋው ይሰጣታል እሱን ትጨርስና ደግሞ ሁለተኛዋ ላም ታልባ እስክትጨርስ ኩባታዋን ይዛ ትቆማለች፣ ልክ እንደመጀመሪያው ትኩሱ ከነአረፋው ይሰጣታል እሱንም ትጠጣለች፣ ለሚታለቡት ላሞች ሁሉ እንደዛ ታደርጋለች፤ ሁል ጊዜ ጠዋት እና ማታ እንደዛ ነበረ የምታደርገው። ትልቅ ሆና ድረስ የእናታችንን ጡት ትጠባ ስለነበረ ሰው እንዳያያት የእናታችንን ቀሚስ በጎን ቀዳ ተደብቃ ነበረ የምትጠባው።
ከእህቴ ጋር በጣም እየተዋደድን አክስቴ ልታሳድጋት ወደ አዲስ አበባ ወሰደቻት። እኔም 6ኛ ክፍል ጨርሼ ወደ አዲስ አበባ መጣሁ። አዲስ አበባም የተለያየ ቦታ ስለምንኖር በተወሰነ ጊዜ ብቻ ነበረ የምንገናኘው። ከ11ኛ ክፍል እስከ ዩኒቨርሲቲ ድረስ ግን አብረን ባንኖርም በጣም እንገናኝ ነበረ።
በልሹ ከቤታችን የአባታችንን ባህርይ የወረሰችው እሷ እና እሷ ብቻ ነች። ለኔ ብዙ ነገር ታስብልኝ ነበረ። የጉብኝት ወረቀት ልካልኝ ሁለት ጊዜ ኤምባሲ ገብቼ ተከልክዬ በሶስተኛው እግዚአብሔር ፈቅዶ ተፈቀደልኝ። በጣም ስለምወዳት ልጄን፣ ባሌን፣ ባጠቃላይ ትዳሬን ትቼ መጣሁ። ከመጣሁ በኋላ በጣም ብዙ ነገር አስተምራኛለች። በተለይ ደግሞ ፍቅርን ሰጥታኛለች አስተምራኛለች። በዚህች አንድ ዓመት ብዙ ነገር፣ እኔነቴን የሚቀይር ምክር መክራኛለች።
በሉሻዬ የእናቴ ልጅ ስላንቺ ልናገር ብል አንድ መጽሐፍ አሳትማለሁ ግን በትንሹ እችን ማስታወሻ ጽፌአለሁ። በልሻዬ አደራ ያልሽኝንም እግዚአብሔር ከረዳኝ ልፈጽም ቃል እገባልሻለሁ። የእናቴ ልጅ ስሄድም ስተኛም ሁሌም እወድሻለሁ። ሀዘኑ በጣም ከበደኝ። ከእግዚአብሔር የመጣ ስለሆነ ምን ማድረግ እችላለሁ።
በጣም በጣም የምወድሽ እና ሁሌም አጠገቤ መሆንሽን ነው የማስበው። ይሄ ክፉ ሞት የሚሉት ለያየን።
ነፍስሽን ከቅዱሳን ጎን ያሳርፍልን።
በጣም የምወድሽ እህትሽ።
Abebe
from
Aldie, VA
wrote on October 31, 2023
at
1:49 am
በልሻዬ ሆዴ አንጀቴ የቤታችን ንግስት፣ የጎጇችን ጌጥ፣ የልጆቻችን ኩራትና ሞገስ ፣ የሰፈራችን ሰብሳቢና መካሪ፣ የዘመድ አውራ፣ አርቆ አሳቢ የጫወታ አዋቂና አድማቂ፣ የኔዋ ንግስት ናት። እንደምንም እየገፋነው ነው። ሃዘንማ ለርሷው ያልታዘነ ለማን ይታዘናል። ውሎአችንም አዳራችንም እርሷን ስለሚያስታውስን በቀላሉ የሚገፋ አይደለም፡፡ ጊዜ የሚፈታው ነው፡፡ ላላፉት 18 ዓመታት በጓደኝነትም በትዳርም ላሳየሽኝ ደግነት፤ እንክብካቤ፤ ክብርና ፍቅር እጅግ አድርጌ አመሰግንሻለሁ፡፡ ያንቺን አይነት ሰው የሚያገኙት እድለኞች ናቸውና፡፡ የኔ ውድ ካንቺ ጋር ለተወሰኑ ደቂቃዎች ጊዜ ማሳለፍ እንኳን መታደል ነው አይደለም 18 ዓመታት፡፡ ለትልቁም ለትንሹም የምትለግሽው ተፈጥሯዊ የፈገግታ ፊት፤ ትህትናና እንክብካቤ እጅግ እጅግ ይማርካል ሁሌም ይናፍቃል፡ እንዴት ታድለሻል እናቴ።
ለቤተሰብሽ ያለሽ ፍቅር እጅግ የተለየ ነው። ሁሉም ሰው ቤተሰቡን ይወዳል ግን ያንቺ ልዩ ነው። ላንቺ ቤተሰብ ማለት ሁሉ ነገር ነው፡፡ የቤታችን ምሰሶ ነሽ፡፡ የዘመድ የወዳጅ አውራ ነሽ፡፡ የምታሳይን ልክ የሌለው ፍቅር አጥንት ሰርስሮ የሚገባ ነው፡፡ እሱን ማጣት ማለት ጥልቅ ሐዘን ነው። እንዴት በቃላት ይገለጻል፡፡ ፈገግታሽ በሥስት የሚያዩን ቆንጅዬ አይኖችሽ ናፈቁን ሆዴ አንጀቴ። ልጆቻችን መቼም ያንቺኑ አይነት ፍቅርና ጥንካሬ የሚላበሱ እንደሚሆኑ ምንም ጥርጥር የለኝም።
አምሳያዋ እንቁዎቹ ልጆቻችን አሁንም እንደ ብረት ጠንክረው ሃዘኑን ዋጥ አድርገው ትምህርታቸውን በበለጠ ጥንካሬ እያስኬዱት ነው። በጆሮ ሹክ የሚላቸው አጽናኙ አጽናንተዋቸዋል እንጂማ ማን ደፍሮ ያናግራቸውዋል። እነሱም የሚያናግራቸው በፍጹም አይፈልጉም። ማሚ የተሻለ ቦታ ናት፣ ከምትወደው አምላኳ ጋር ናት ተባሉ፣ ተማሩ አመኑ አለቀ። የስድስት ዓመቷ ሜላት አንድ ቀን Mommy is in a better place ብዬ ገና ሳልጨርስ Everybody is saying that. Can you please stop saying that? I know that she is in a better place. You make me sad when you keep talking to me like that. ካለችኝ ቀን ጀምሮ የምናገረውን ቆጠብ አድርጌዋለሁ። ብርቱ ናቸው ልጆቹ። ለነገሩ ስለሞቷ ከሰው ጋር ማውራት እስከ አሁን ለኔም ይከብደኛል። ይነዝረኛል፡፡ ሁላችሁንም አሁንም ከልብ እናመሰግናለን፡፡ እኔም፤ ልጆቹም መላው ቤተሰብ ደህና ነን አታስቡ፡፡
እግዚአብሔር የአስካለ ጊዮርጊስን ነፍስ ከቅዱሳኑ ጋር ያሳርፍልን::