37 entries.
Tamiru
from
Addis Ababa
wrote on August 31, 2024
at
7:33 am
I am in shock learning the passing of Beletech.
While I was active online most of the past Yr, it didn't came to feed nor learned from a common freinds about her passing. Literally learned this saddening news few min ago.
We met in 2008 at Maharishi University of Management and became freinds and I like her respectful and friendly attitude since our first encounter.
Really unfortunate leaving so early. I wish continued comfort to her loved one. I am happy to also learn that she will be survived by her kids and family.
Rest in Peace!
Birhan Demeke
from
Chantilly
wrote on December 13, 2023
at
9:38 pm
ለምወድሽና ለማከብርሽ ውዷ እህቴ፣ ጓደኛዬ፣ ዘመዴ፣ ቤተሰቤ ሁሉ ነገሬ በልሻዬ እንዴት ነሽልኝ? እኔ ሁሌም ትናፍቂኛለሽ፣ ጓደኞችሽንና የሚያውቅሽን ሁሉ ባየሁ ቁጥር ትዝ ትይኛለሽ። በልሻዬ ሳቅሽ፣ ጨዋታሽ፣ ቁም ነገርሽ ሁሉም ነገር ናፈቀኝ። በልሻዬ አንድ ጥያቄ ልጠይቅሽ በጣም የምትወጂው የምትሳሺለት ውዱ ባለቤትሽ አብሻን እና ሁሌ አዉርተሽ የማትጠግቢያቸውን ልጆችሽን እንዴት አመንሻቸው እንዴትስ አስቻለሽ? እንዴት ቻልሽው?
በልሻዬን የማውቃት የዛሬ 16 ዓመት ነው። ከተዋወቅን ጀምሮ እህቷ ነኝ እህቴ ነች ቅርበታችንም እንደዛው ለሰው ስታስተዋውቀኝ እህቴ ናት ብላ ነው የምታስተዋውቀኝ እኔም እንደዛው። በጣም ብዙ ነገር እናወራለን እንስቃለን ቁም ነገርም ከተጀመረ እንደዚያው በጣም ጨዋታ ታውቃለች፤ ለሁሉም እንደ አቅሙ መጥና ታቀርባለች። በልሻዬ ልዩ ነች። የሰው ደስታ በጣም ያስደስታታል። አንቺን ማጣት በጣም ከባድ ቢሆንም ግን የእሱ ፈቃድ ስለሆነ ተቀበልነው። ሰርጋችንም በአንድ አመት ነበር። ድጅ እና አብሻ አንድ አካባቢ ይኖሩ ስለነበር ሁሌ ቤታቸው እንደጋበዙን ነው። ሁሌም መገናኛችን እነ በልሻዬ ቤት ነበር። ኢትዮጵያም እያሉ ቤታቸው የሁሉ መሰብሰቢያ የሁሉ መጠጊያ የአብርሃም ቤት ነበር። እዚህም ሲመጡ ያንኑ ይዘው ነው የመጡት።
በልሻዬን ካወኳት ጀምሮ በጣም የዋህ፣ ደግ፣ ሰውን በጣም አክባሪ ነበረች። ወደዚህ አገር የት/ት እድል አግኝታ ስትመጣ በጣም እጨነቅ ነበር። አብሻን በጣም ስለምትወደው ተለያይተው አንድ ቀንም ታድራለች ብዬ አስቤ አላውቅም ነበር ግን በጣም መልካም ሰው ስለሆነች ውድ ባለቤቷንም ቶሎ አጠገቧ አደረገላት እኔም በመለያየታችን በጣም ባዝንም አንድ ቀን እንደማገኛት ተስፋ ነበረኝ በልሻዬንና አብሻን በጣም ከመውደዴ የተነሳ ወደዚህ ሀገር ለመምጣት ዲቪ እንኳን አምልጦኝ አያውቅም ነበር። ደጅ ወዲዚህ አገር ለመምጣት ቪዛ ማግኘቱን ለነበልሻ ስንነግራቸው “ደጅ በል ወለም ዘለም የለም እኛ ጋር ከች ነው።” ሲሉን መቼም የማልረሳው ደስታ ነበር የተሰማኝ፤ እነበልሻዬን በድጋሚ የማግኘት ምኞቴም እግዚአብሔር ፈቅዶ ተሳካልኝና እኔም ቶሎ መጣሁ።
እዚህ አገር ከመጣሁ በኋላ ቅዳሜና እሁድ አነ በልሻዬ ጋር ነን ሁሌ ተደስተን ነው ወደቤታችን የምንመለሰው። ለበዓልም አብረን ነው የመናሳልፈው። ከተገናኘን ቶሎ መለያየት አይታሰብም። ለበዓል እንዲሁ ለመጠየቅ ስንሄድ ወደ እናትና አባቴን ለማየት እንደምሄድ ነው የሚሰማኝ። በልሻዬ የምወደውንና የማልወደውን ታውቃለች ለሌላሰው እንኳን ባያስፈልግ ለእኔ ብቻ ሲባል ዶሮ ይሰራል፤ ሁሉን እንደጸባዬ ነው የምትሆንልኝ።
በልሻዬ ሳቅሽ፣ ጨዋታሽ፣ ምክርሽ ቁምነገርሽ ናፈቀኝ። በልሻዬ ለኔ አንድ ሰው ሳትሆን ሁሉ ነገሬ ነበረች። ስለ ልጆቻችን፣ ስለ ህወታችን ባጠቃላይ ስለሁሉም ነገር የምናወራው ምክሯ ከአእምሮዬ አይጠፋም። ህመሙ ከተከሰተ በኋላም ህመሟን በውስጧ ነው፤ ሰውን ማስጨነቅ አትፈልግም እርሷ ግን በህመም ውስጥ ሆናም ለሰው ትጨነቃለች ሰው ፈገግታዋን እንጂ ህመሟን አያይም። አንድ ቀን እኛ ቤት መጥታ ትንሽ ላወራት እድሉን ሳገኝ በልሻዬ እንዴት ነሽ አሁን የእኛ ነገር ሁሌ መሳቅ ብቻ ነው ስላት ሳቅ አለችና “እግዚአብሔር ይመስገን ዛሬ መድሃኒቴን የምጨርስበት ቀን ነው በጣም ደስ ብሎኛል። ብርሽዬ በህይወትሽ ደስታም ሃዘንም ይኖራል ሁሉንም እንደ አመጣጡ ጠንካራ ሆነሽ ማለፍ አለብሽ እኔ እዚህ አገር ከመጣሁኝ በኋላ ወንድሜን በሞት አጥቻለሁ በወቅቱ በጣም ነው የተጎዳሁት ግን አለፈ ብዙ ነገር አስተምሮኛል ይሄም ህመም ሲመጣ ያልፋል ተመስገን ብርሽዬ” አለቺኝ። እኔም በልሻዬ አንቺ ጠንካራ ስለሆንሽ የእግዚአብሔር በረከት አልተለየሺም አልኳት። የዛን ቀን አሁን መድሃኒቴን ከጨረስኩ ስፖርቴን እጀምራለሁኝ አለችኝ። የማልረሳው ቀን።
ስንደዋወል ሁሌም በልሻዬ ስላት “ወዬ ብርሽዬ ነፍስ ልክተትሽ በኪሴ” ነው መልሷ በየትኛው ስላት በሁሉም ትለኛለች፤ በልሻዬ እንደዚያ ናት ስትወድ ሁለመናዋን ነው የምሰጠው። በልሻዬ አንቺን መርሳት ከባድ ነው። እስካሁን ደረስ ያለሽ ያለሽ ይመስለኛል፤ መሄድሽን ተቀበልኩት እንጂ ውስጤ አላመነውም። እንዴት ብዬ ልመነው? ሁሌም እወድሻለሁ አከብርሻለሁ በልሻዬ የኔ ቆንጆ።
በልሻዬ ስትፈጠር ልዩ ሆና ነው የተፈጠረችው። ደግነቷ፣ የኋህነቷ ለሰው የምትሰጠው ፍቅር ወደር የለውም። ሳውቃት አንድም ቀን፤ በህመም ውስጥ ሆና እንኳን ተከፍታ ወይም ዝም ብላ አይቻት አላውቅም በልሻዬ እንደዚያ ናት በእርሷ ዘንድ ለሰው መልካም እንጂ ሌላ ነገር አይገኝም።
በልሻዬ የኔ ቆንጆ፣ የኔ ደግ፣ የኔ አዛኝ፣ የኔ ሩህሩህ እግዚአብሔር ነብስሽን ከደጋጎቹ አባቶቻችን ከቅዱሳን ከጻድቃን ሰማዕታት ጋር የኑርልኝ።
አሜን።
አብሻዬ ያደረከው ነገር ሁሉ በጣም ደስ የሚል እሷም ደስ የሚላት ነገር ስለሆነ አንተን እጅጉን አመሰግናለሁ፤ አከብርሃለሁ። የተጀመረው የበልሻዬ ፋውንዴሽን ወደፊት አድጎና ትልቅ ደረጃ ደርሶ አንተም የምትመሰገንበት ነው። አንተ በርትተህ ስላበረታሃን እናመሰግናለን። ያንተ መጠንከር የለጆችህም የኛም ብርታት ነው። እግዚአብሔር ብርታቱንና ጥንካሬውን ያድልህ፤ በርታልን እንወድሃለን፤ እናከብርሃለን አብሻዬ የኔ ወንድም።
አሜን።
alemnesh
from
addis abeba
wrote on November 28, 2023
at
8:48 am
በልሻዬን ያወኳት ከወንድሜ አብሻ ጋር በጓደኝነት ብሎም በትዳር አንድ ላይ መኖር ከጀመሩ ጊዜ አይስቶ የማውቃት ሲሆን ካወኳት ቡኋላም በልዬ እጅግ በጣም የተለየች ልጅ፤ ደግ፤ አዛኝ፤ ሩሩህ ፤ተጫዋች፤ አጫዋች፤ እንዲሁም አስተዋይ እህታችን ነበረት በማለት የበልዬን ነገር ማዝጋት አይቻለኝም እሳ ከቃለትም ከነገሮችም ከድርጊቶችም በላይ ናት በልሻን መግለጽ ለኔ እጅግ በጣም ይከብደኛል እሳ ሁል ጊዜ ስራ ላይ ነበረች በጫወታም መሀል ቁምነገር ነበራት በቁምነገርም ጉዳይ ሰውን ታንጻለች ሁሌ ከህሊናዬ የማይጠፋው ምክራ ያለሽ ጊዜ ዛሬ ነው ነገ የራሱ ነው አሁን ጊዜ ካለሽ መሆን፣ ማድረግ ያለብሽን አድርጊ በማለት ትመክረኝ ነበር በልሽዬ ልክ ናት ነገ የኛ እንዳልሆነች ቀድማ ተረድታለች ለዚህም ነው የ80 አመት የቤት ስራ እሳ ቀድማ የሰራችው ይገርማል እወቅ ያለው በ40 ቀኑ እንደሚባለው በልሻ ድንቅ ልጅ ነበረች ደግሞም ሞት ሀያል መሆኑን በእሳ አየሁ በልዬ ሁል ጊዜ ለሰው ደስታ መፍጠር ነበር ፍላጎታ በልሻ ልጆች በጠም ነው የምትወደው ከሀገር ከመውጧቷ በፊት እሁድ ቀን ለሊት ተነስተን ቦሌ መዳኒአለም ለማስቀደስ ሄደን ቅዳሴው ተጀምሮ እስከሚልቅ እሳ ከፊታችን የነበረውን ህጻን ስታቅፍ ስታጫውት ቅዳሴው አለቀ አዶም ሁሌ ትላለች ከአዋቂ ጋር ከመሆን ይልቅ ሰው ቤት ጥር ተጠርተን ስንሄድ እንኳን ወደ ልጆች መጫወቻ ክፍል በመሄድ ከልጆች ጋር ማሳለፍ ነው የሚያስደስታት ትል ነበር፡፡ ለልጆቼ ምንም ሳልላት ነበር የሚያስፈልጋቸውን የምትልክላቸው የእውነት አክስት ነበርሽ፤ የእውነት እህትም ነበርሽ፤፤ እውነቱን ልንገርሽ ይህ ተግባርሽ የውስጥሽን ንጽህና ነው ያሚያሳየው የኔ ውድ እህት በልዬ፡፡ ግን ሁሌም የአምላክ ስራ በጣም ድንቅ ይለኛል ለምን እላለው ደግሞም መለስ እልና የእሱ የእጆቹ ስራ ናት እልና እፅናናለው፡፡
አየሽ በልዬ ስላች ሁሉም አንድ ቋንቋ ነው የሚያወራው ምን አይነት መታደል ነው በዚህ ሁሉ ሰው ልብ ውስጥ መኖር፣ መመላለስ በጣም ያስቀናል፡፡
ኢትዬጽያ መጥተው በነበረ ጊዜ አብሻ ቀድሞ ስለተመለሰ እሱን ሸኝተን ከኤርፖርት ስንመለሽ እሳ እየነዳች እኛ መንገድ እየመራናት ስንሄድ ለሊት ስለሆነ መንገድ ስተን ነበር እሳ ግን አላወቀችም ነበር ምነው መንገዱ ራቀ ችግር የለውም መንገዱ ከጠፋባቹ ስንሄድ እናድራለን እያለች ስትቀልድ ቆይታ እውነት እንደጠፋብን ስታውቅ እንዴዴዴዴደ እኔ እኮ ስንሄድ እናድራል ያልኩት ለቀልዴን ነው የምር አደረጋቹት እንዴ እያዳድሽ የነዳጅ ትከፍያለሽ ያለበለዚያ አልነዳም በማለት አጫጭታን ነበር፤፤
የኔ ውድ በልሻዬ ነብስሽ በሰለም ትረፍ
አምላኬ ሆይ የአስካለ ጎርጊስን ነብስ በሰላም አሳርፍ
ከደጋግ አባቶቿ እቅፍ አኑርልን አሜን
ያንቺው እህት አለም
Solomon Balcha
from
Silver Spring
wrote on November 26, 2023
at
11:09 am
እኔ በልሻዬን በቃላት መግለጽ ባልችልም ለቤተሰብ ያላት ጥልቅ ፍቅር እና ለሰው ሁሉ ያላት ፍጹም ፍቅር በጣም የሚገርም ነበር፤ እሷን ለየት የሚያደርጋት ነገር ጥንካሬዋ ለሁሉ ምሳሌ ነበር ለምታውቀው ሁሉ የምትመኘው ከስዋ የተሻለ ሌሎችን ለማበርታት እኔ የሰራሁትን አንተ አያቅትህም ትል ነበር፤ ደግነትዋ የምር ነበር እቤት ስንሄድ ሁሌም ወደ በር መጥታ ነበር የምትቀበለን ሁሌም በጫወታ እያዋዛች ሰውን ትመክር ነበር ። ሌላ ነገር ደግሞ የእምነት ጥንካሬዋ እና በእግዚዓብሄር ላይ ያላት ፍጹም እምነት በጣም የተለየ ነበር፣ በጠና ታማ እንኳን ታመሰግን ነበር ፤ በልሻዬ በማንም በፍጹም ሊተካ የማይችል ጉድለት ጥላብን ሄዳለች፣ በቃ ከሷ ውጪ ማንም ሊሞላው የማይችለው -ለሷ ብቻ የተሰጣት ልዩ ስጦታ ነበራት። ይሀው ቤት በሄድኩኝ ቁጥር ያንን ከውስጥ የመነጨ ልዩ ፈገግታ እየናፍቅኩ ቤት ደርሼ እመለሳለሁ፣ የበልሻ ነገር ቢፃፍ ኣያልቅም። እግዚዓብሄር የወደደውን አደረገ፤ ነፍስሽን በገነት ያኑርልን፤ እንወድሻለን ።
Gezahegne Yirefu
wrote on November 25, 2023
at
12:00 am
በልሻን መጀመሪያ ያገኘኋት አይዋ ስቴት ማስተርስ ስንማር ነበር። እዛ ስንማር በስቴቱ ምንም ዓይነት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤ/ክ አልነበረም። በሳምንት አንድ ቀን ዓርብ ዓርብ የቤ/ክ የሆን ልጆች ተሰብስበን በማሕበረ ቅዱሳን የግቢ ጉባኤ እናካሒድ ነበር። ክሌላ ስቴት የሚያስተምሩንን ትምህርት የምንከታተለው ስልክ ከፍተን ስፒከር ላይ በማድረግ ነበር። የፕሮግራም አስተባባሪው እኔ ብሆንም የሚገርመው ነገር የሚረባ ነጠላ አልነበረኝም። በልሻም በዚህ ፕሮግራም ላይ ከሚሳተፉት ተማሪዎች አንዷ ነበረች። መጀመሪያ ቀን በልሻ ካየችኝ በኋላ በሚቀጥለው ዓርብ ምን የመሰለች ሽሪሚሪ ፣ አራት የመስቀል ጥልፍ ያለባት ነጠላ ጋቢ ሰጠችኝ። ስጦታዋ ቢከብደኝም በጣም ነበር የተደሰትኩት። እርግጠኛ ነኝ ከኢትዮጵያ ስትወጣ በወቅቱ በውድ የገዛችው ወይም ሰው ማስታውሻ ብሎ የሰጣት ነው። ከት/ቤቱ እስክንወጣ ስጠቀምባት ቆይቼ እቤቴም ሁል ጊዜ ከ10 ዓመት በላይ ጸሎት የማደርሰው በሷ ነበር። ብጭቅጭቅ ብላ ልጆቼ ሁሉ ለምን እንደማረጋት ይጠቁኝ ነበር። ሁልጊዜም ያደረገችው ነገር ይገርመኝ ነበር። ከሁላችንም ጋር ተግባቢና የምታስቀን ነበርች። ከበልሻ ጋር በተለይ እዛ ት/ቤት እያለን ሜኔሶታ ስቴት የትንሳኤን በዓል ለማክበር ተሰብስበን ሔደን የማይረሳ ጊዜ አሳልፈናል።
በልሻ (አስካለ ጊዮርጊስ) በዚህ ዓለም ፍሬ እንዴት እንደሚፈራ ጠንቅቃ ያወቀችና ክርስትናን የኖረችው እህታችን ነች። ከአጠገባችን ብትለየንም እንደሷ የክርስትና ፍሬ አፍርቶ ወደ ጌታ ደስታ መግባት በእውነቱ መታደል ነው። አቤንና ልጆቹን እንዲሁም ቤተሰቦቹን ሁሉ ልዑል እግዚአብሔር ይጠብቅልን። የአስካለ ጊዮርጊስን ነፍስ በአጸደ ገነት ያኑርልን የጸሎቷም በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን!
Hiwot Selame
from
Addis Ababa
wrote on November 22, 2023
at
9:36 pm
I still can't believe that you really are gone my dear sister. Belsha ጓደኛዬ ብቻ ሳትሆን እህቴ፣እናቴ፣መካሪዬ፣አሳቢዬ፣ተንከባካቢዬ፣ሙሽራዬ ናት።ከ elementary school ጀምሮ high-school GCA የበለጠ ደግሞ Mekelle University
ያላት የትምህርት ትጋት በተለይ Math ላይ ያላት ፍቅር አይረሳኝም ።በተለይ በጊቢ በቆይታችን ሁሉ ነገሬ ነበረች።እናቴ ነበረች።ከራበኝ አብልታ፣ከተጨነኩ አረጋግታ ብቻ ያንን ጊዜ ያለፍኩት Belsha በመኖሯ ነው።
ከሁሉም የሚገርመኝ 3rd Year እያለን አልጋዋን ያለስስት ሰታኝ without any complain አጋርታኝ 1አመት ሙሉ ራስጌ እና ግርጌ ነበር የምናድረው።በእውነት ይህንን በልሻ ባትሆን ማን ያደርጋል ።
ደግሞ ሌላ የሚገርመኝ የሰው ሁሉ ችግር እንደራስዋ የሚያሳስባት ናት።ባላት አቅም ሁሉ መፍትሄ ለማምጣት ወደ ኋላ አትልሞ።ሰውን ማረጋጋት ስትችልበት። ይገርመኛል ጊቢ እያለን በሆነ ነገር ተጨንቄ ለበልሻ ካወራኋት እንዴት እንደሆነ አላውቅም ከአፍታ በኋላ እራሴን እየሳኩ ነው የማገኘው።
ከሰው ሁሉ ጋር ያላት መግባባት ይገርመኛል።በልሻ ጋር ይሄኛው እንዲህ ነው ያኛው እንዲያ ነው ብላ የምታገለው ሰው የለም።ከሁሉም ተግባብታ፣ በፈገግታ ተሞልታ ፈገግታዋን ታጋባለች።
ሁሌም ጠንካራ ሰራተኛ ናት። ትምህርት ላይ፣ትጋት ላይ ቀልድ የለም። ሀይማኖት ፣አገልግሎት ለበልሻ ሕይወቷ ነው። የበልሻ ጓደኛ ሆኖ እለት እለት በቤተክርስቲያን አፀድ ያለመገኘት፣ጉባኤ፣ፅዋ፣ ፀሎት ያለመሳተፍ የማይታሰብ ነው።የፈተና ወቅት ሆኖ እንኳን ብንጨናነቅ በልሻ የተሻለውን መፍትሔ ታመጣለች። cafe or library ስንሄድ ነጠላችንን ይዘን ሄደን በዛው ወደ ቤተክርስቲያን መሄድ ወይም ብቻ የሆነ ሀሳብ።እንጂ ምከንያት እየደረደሩ ከደጀ ሰላሙ ማፈግፈግ የለም።
አገልግሎት ሕይወቷ ነው። በጎ አድራጎት ክፍል እውነትም ከእርሷ ጋር የሚሄድ የአገልግሎት ክፍል ነበር።ሁሌም ሰውን ማገዝና ማገልገል ደስታዋ ስለነበር።ይገርመኛል ከተማ ያለ የሆነ ቤተክርስቲያን ሄደወ፣ደጀሰላሙን ጠርገው፣አልባሳት አጥበው ሲመጡ የነበራት ወሰን የለሽ ደስታ ይሄ ነው አይባልም።
ከሀገር ከወጣችም በኋላ የሰው ነገር አይሆንላትሞ።
ስለሁላችንም ትጨነቃለች ።
ብቻ ስለበልሻ ተነስቶ በዚች ቃል ብቻ ተገልጾ ሊያልቅ አይቻልም።
ሁሌም እወድሻለሁ ።ሀዘንሽ እጅግ አስደንጋጭ ነው።ህመምሽን እንኳን ሳናውቅልሽ። ከሳምንት በፊት ነበረ መታመምሽን ያወኩት።በጣም ያስደነግጥ ነበር።በንጋታው አቡነ እጨጌ ዮሀንስ የአመት ንግሳቸው ነበርና ታምራታቸውን ስለሰማሁ ሄጄ ተማፀንኳቸው እንዲዳስሱሽ።
ብቻ ሁሉም የፈጣሪ ፍቃድ ነው። ምን እንላለን።
አስታውሳለሁ ከአቤ ጋር ከመጋባታችሁ በፊት በጓደኝነት አንድ ቀን ስትነግሪኝ አብረን ውለን ነገ እንደምንገናኝ እያወኩ እራሱ ቅድስተ ማርያም ጋር ቻዎ ስንባባል አይኔ በእንባ ይሞላል የሁለታችንም ትይ ነበር በናፍቆት።በጣም የሚገርም ፍቅር ነው።
እናም አቤ ሀዘኑ ላንተም ለሁላችንም ከባድ ነው።ነገርግን Belsha foundation መቋቋሙ መፅናኛችን ነው። በቻልነው ሁሉ ለመደገፍ ከጎንህ ነን።
ለአቤ & for the beautiful angels ለመላዉ ቤተሰብ፣ወዳጅ፣ዘመድ፣ጓደኛ ለሁላችንም እግዚአብሔር መጽናናትን ይስጥ፣የእህታችንን ነብስ ከደጋጎቹ ጋር ያሳርፍልን። አሜን!!!
Nardos
from
Aldie
wrote on November 19, 2023
at
5:01 am
To be honest, I didn’t want to write anything because It’s still hard for me to accept Belisha is gone forever.
When we met Belisha 11 years ago, the first thing she said to us was “please come to our house and let’s have coffee”. Who would say that on the very first day you met them except Belishaye!
She had an amazing personality, so kind and caring, always there for those in need, a good friend to talk about anything, ሰው በልቶ የሚጠግብ የማይመስላት, ቁምነገረኛ and great sense of humor (I miss all the funny ጨርቆስ stories)
Belisha was there for me when I was in a dark place after my dad’s passing. Whenever I went to visit her, she worry about how I am doing even from the hospital bed. She cry with me and then በቃ ብላ ደግሞ መቆጣት ትጀምራለች::
She hides her suffering and comfort others.
Merso is not going to be the same without Belisha. It’s a big loss for all of us.
I know she is in a better place but It’s not easy to accept that she is gone forever.
I struggled using past tense when writing this to express a little about who Belisha was for me.
Belishaye, May your soul rest in eternal peace and God gave all of us comfort!
Bethel Abebe
from
Aldie, VA
wrote on November 17, 2023
at
11:08 pm
Let’s say my mom is carrying some candy in her hands. You walk past her, and glance at the candy for one second. When she sees you looking at her candy, instead of saying, “it’s mine” or “You can only have a little”, she asks you, “do you want it?”, and she hands you everything that was in her hands. That’s the type of person she was.
My mom was a very smart, beautiful, social, and kind human being. I’ve looked up to her and my dad, proud to have a mom like her. Some people at school or church would sometimes complain a little about how strict their mom was, and I would always brag, saying I had an easygoing mom.
She was so good with people. She meets strangers at work, at the mall, on the road, it doesn’t matter, but she would get them laughing in minutes. She would also get my friends to play games with her, which was really hard. I remember, there was a party, and her legs started hurting, so she decided not to go. I was tired, so I decided not to go either. My mom probably got 30 phone calls in just the first ten minutes. All her friends were asking her, where are you? Why aren’t you coming, I can give you a ride if you don’t have one. By the end of the hour, me and my mom were already at the party, and you could hear the adults laughing at my mom’s jokes from the basement.
My mom was also super smart. She would always make me sit with her and practice math. I would always get annoyed at the time, but I’m so thankful now. She had a very good memory. My dad told me how they went to have lunch with some old friends, and my mom brought some formula she learned back in high school. My dad and their friends had no idea what she was talking about, as they barely remembered what they learned in college. She also remembers the whole periodic table from seventh grade, which she taught me, and I forgot by the end of the week.
She always thought about us. Her friends, her kids, her family in Ethiopia. My aunt needed money to start a business, and my mom sent her money for it, even when she was sick. Every time she was in pain, or when she was tired, she would never show it until we were out of the room, thinking about us. Whenever her friends came to visit, she would talk and laugh with them, even when she didn’t feel like it.
My mom was an amazing person that everyone loved and we’ll all miss, but it’s better to know that she’s not suffering anymore and she’s in a better place. Mommy, I love you so much, and I promise I will try to be just as hard-working as you. May you rest in peace and love.
Yarsema Girma
from
Chantilly
wrote on November 7, 2023
at
5:26 pm
There are times when I wonder, why would God do this? The most common answer would be "God has a reason for everything" so when something happens that I don't want, I try to see it from God’s reason perspective, but this time, I couldn't, at first, I thought there was no reason, but I had to put my trust in God, knowing that he must have a very good reason. Because every time a kid talks to Beti or Amy about Belisha, these words would ALWAYS be said; 'Belisha was like a 2nd mom to me.' This was true, she was like a mom to every kid who knew her, she was so kind, sweet, and cheerful, her characteristics could go on and on. She was so lovable that people who didn't know her well bawled their eyes out the day after she passed away. She touched many lives with her kindness and generosity. She was a fantastic person, and even if we don't see her again till we meet her in heaven, she will be in our hearts and watching over us.
I’ve known Belisha for all my life, my parents met both Abe and Belisha and we lived with each other for months, while they were living together, my dad would tell me how he and Belisha would fight each other for fun, how they would talk about random things and have fun all night, both Abe and Belisha and my parents became good friends and that’s how Beti and I became friends.
Even if Belisha is gone, she is in a better place. The day Belisha passed away, I felt like a truck ran over me. Thankfully, Hanicho helped me. She told me that losing someone you love is never easy, and it’s natural to feel grief and sadness. It’s okay to cry and express your emotions because that’s part of the healing process. You don’t have to pretend everything is fine, because it’s not. You have the right to mourn and honor her memory. I later gave this advice to others. Because nobody is alone in this difficult time, we all have each other’s back, no matter what happens. We all miss Belisha, but she is in a better place now. Belisha will always be remembered and cherished.
Abe; you’re not going through this alone, you have a family, a community to help you and have your back.
Beti, Amy, and Melat; if you ever need comfort or need a shoulder to cry on, we’re always there for you.
May God
Matthew 5:4 - Blessed are those who mourn, for they shall be comforted.
Henok Habtamu
from
Dublin, Ohio
wrote on November 5, 2023
at
3:42 pm
በልሻን በወንድሜ በአቤ በኩል ካወቅሗት ብዙ አመታት ሆነዋል። እጅግ ግሩም እህቴ እንዲሁም እጅግ ግሩም የጆቼ ክርስትና እናት ነች። በልሻ ከልጅ እስከ አዋቂ፥ ከሴት እስከ ወንድ፥ ከዘመድ እስከ ባእድ፥ ከሁሉ ጋር መሳቅ መጫወት መለገስ ማብላት ማጠጣት ነው ስራዋ። ንፍገት ብሎ ነገር አልፈጠረባትም። ከልጆቼ ጋር (የሷ ክርስትና ልጆቿ) ጋር ለሰዓታት በጨዋታ እያዋዛች ስለህይወት፥ ስለሃይማኖት፥ ስለ አለማዊ ት/ት፥ ታስተምራቸው ነበር።
ባወቅሗት ዓመታት ሁሉ በልሻን ስትስቅ ፥ ስትጫዎት፥ ስትለግስ ነው የማውቃት። ሆስፒታል እንኳን ሆና በነዛ ከባድ ሰዓታት ለደቂቃም ሳቅና ጨዋታ ተለይቷት አላየሁም። ከባድ ህመምን ችሎ፥ በዚህ አለም ያለ ቆይታ እንዳለቀ ተነግሮ በተለይ ከወለዷቸው ልጆችና ከሚወዱት የትዳር አጋር ጋር ለመጨረሻ መለያያ ጊዜ እንደደረሰ እያወቁ እንዴት መሳቅ መጫወት ይቻላል?!! ይገርማል። በልሻ ግን ታደርገው ነበር። ልዩ ተሰጥኦ። እህቴን በልሻን ካወቅሗት ጀምሮ ሁለት ጊዘያት ብቻ ሳቅና ጨዋታዋን አላየሗቸውም፥ ፩ኛ) ለመጨረሽ ጊዜ በስልክ ያወራሗት ቀን። በዚች እለት በልሻየ እንዴት ነሽ? ስላት እንደወትሮው ሰላም ነኝ ሄንዬ ትለኛለች ብዬ ስጠብቅ ከእህቴ የሰማሁት መልስ ግን “ሄንዬ አሁንስ አቃተኝ” የሚል ነበር። አንዳች መብረቅ እንደመታው ደነገጥሁ። ምንም መመለስ አልቻልኩም ስልኩን ዘጋሁት። ሰውነቴ ተብረከረከ። ሰውመሆኔን ጠላሁት ምክንያቱም እህቴ በዚህ ሁኔታ ሆና ምንም መርዳት ባለመቻሌ። ፪ኛ) በልሻ አምርራለች:: “አቃተኝ” የሚለውን ቃል እንኳን መናገር አቁማ የዚች አለም ጉዞዋን ጨርሳ ለስንብት መድረክ ላይ ሆና ያየሗት ዕለት ነበር። በሌ እነዚህ ሶስት የህይወትሽ ጊዜያት እስከ ሂዎቴ ፍጻሜ አብረውኝ ይኖራሉ። ውድ እህቴ በሰላም እረፊልኝ። ለልጆችሽ፥ ለአብሻ፥ ለመላው ዘመዶችሽ ሁሉ ፍጹም መጽናናትን ይስጥልን።
Dejenu
from
CHANTILLY
wrote on November 5, 2023
at
2:34 pm
In the light of cherished memories, we think of you today,
To honor a dear friend who's now gently taken away.
In laughter and in sorrow, our hearts forever intertwined,
We celebrate the bond we shared, a love that's so defined.
Though you've embarked on a new path, leaving footprints in our hearts,
We'll keep your spirit alive, as each memory imparts.
As tears may flow like rivers, and grief may cloud our sight,
We'll remember you with gratitude, your love's eternal light.
Belisha's laughter was a melody, her smile a radiant sun,
In every moment shared, her warmth was never undone.
We'll find the echoes of her laughter, the twinkle in her eyes,
A bond that death cannot erase, as time unceasingly flies.
In the garden of our memories, you'll forever bloom and grow,
A cherished friend, a precious soul, the love we'll always know.
Rest now in eternity's embrace, in a realm so pure and deep,
My dear Belisha, in God's own care, may your soul forever sleep."
Belishaye, you packed me lunches for my library days,
A memory destined never to fade; in my heart it lays.
Just like my mother did in my childhood days,
Your kindness and care, like a guiding blaze.
Through new days and uncharted realms unknown,
You stood by my side; a light brightly shone.
Overcoming barriers and cultural divide,
You were my anchor, my unwavering guide.
For holidays, we had a cherished tradition to unite,
But now, dear Belishaye, as you journey far and wide.
We hold your memory close, as we bid you farewell,
Rest in eternity's embrace, like a shining star, we compel.
My dear Belisha, under God's gentle sweep,
May your soul find tranquil slumber, in peaceful, eternal sleep.
የሸዋጌጥ በቀለ
from
Aldie, VA
wrote on November 5, 2023
at
2:23 pm
ምስጋና ለበልሻ
በልሻ እንዴት ነሽ?
አዲሱን ዓመት እንዴት አሳለፍሽው?
በጠባቧ ቤት? እኛስ አለን ብዙ ነገር ጎሎብን፣
ሳቅና ጨዋታሽ ጠፍቶብን በእንባ ተሞልተን።
በልሻ ቤት የገባች ዓለም በሰላም አትወጣ
በረጅም ብርጭቆ ኮሶ ሳታጠጣ
የካናዳ ዘመድ ባለህበት እርጋ
የበልሻ ቤት ተዘጋ በጠጋ
የዲሲውም ዘመድ ባለግበት እርጋ
የበልሻ ቤት ተዘጋ በሳጥን
የኢትዮጵያ ዘመድ ባለህበት እርጋ
የበልሻ ቤት ተዘጋ ባፈር
አልዲ ላይ የወረደው ናዳ
በልሻን ነው እንጂ ሌላ ሰው አልጎዳም።
ምነው አባቶች አታልቅሺ ይሉኛል
እኔ ላልቅስ እንጂ ውስጧን ስለማውቅ፣
ሦስት ዓመት ሙሉ መቀስ ለበላት።
በልሻ አትመጪም ወይ ቤተሰብ አትናፍቂም ወይ?
በየት ልምጣ ካንሰር ቆረጠብኝ እጣ
አበበ በጣም አትዘን ሚስት የሞተችበትን ጠይቀህ እደር
ምንም ቢመሽብኝ እድንጋይ ሥር ባድር
የኔ በልሻ ሳልልሽ አላድርም
ኧረ መሸ ይህ ቀን ወዳጅ ወዳጁን አሸሸ
የኢትዮጵያ ደሀ እሪ ብልሽ አልቅሽ
በልሻ ሞታለች የሰንበት ምሳሽ
የበልሻ እኅት በጣም አትዘኚ
እኅት የሞተባት ጠይቀሽ እደሪ
የበልሻ ልጆች በጣም አትዘኑ
እናት የሞተባቸውን ጠይቃችሁ እደሩ
አባቶች በጸሎት ዶክተር በመድኃኒት
ቤተሰብ በገንዘብ እንተባበር
ይህንን ካንሰር እናጥፋ ከሀገር
አስቸግሮናል ቆንጆ እየቀጠፈ
የበልሻን ወርቅ አምጡላት አብራችሁ ቅበሩት
እርግፍ ይበል እንደባለቤቱ
የበልሻን ልብስ አምጡላት አብራችሁ ቅበሩት
እርግፍ ይበል እንደባለቤቱ
ምነው አባቶች ሲያለባብሱሽ ሲያረጉሽ ሙሽራ በቤተክርስቲያን፣
ምነው ዲያቆኖች ሲያለባብሱሽ ሲያረጉሽ ሙሽራ
አትያቸውም ወይ ልጆቼን ላሳድግ?
መስከረም ሲመጣ አበባ ያብባል፣
የዘንድሮው ዝናብ ልክ አይደለም መሰል
በልሻ የአበበ አበባ ስትከስም አየኋት።
ቦብሻ ልጄ ልጄ ብለው ብትንገበገቡም
እንጀራ ነው እንጂ ልጅ የእዝን አይገባም
ምድር አትቆጪ ቀስ ብዬ እረግጣለሁ
ነገ ታች በታች መሆኔን አውቃለሁ።
አልቅሰን አልቅሰን ልብሳችን ርሷል
ካምናው ክረምት የዘንድሮው ብሷል
እንዲያው ደፋ አለች ያች ዝሆን ምን ሆና ይሆን?
ወንድሞቼ ቄስ ገብረሥላሴ፣ ቄስ አውግቸው፣ ገብረሕይወት ንጉሴ
እንኖራለን በእግዚአብሔር ቸርነት
እናንተ ባፈር ውስጥ እኔ በስደት
በልሻ ላጠፋሁት፣ ለተሳሳትኩት ነገር ሁሉ ይቅርታ!
Girmay
from
Centreville
wrote on November 5, 2023
at
1:31 am
It is an extremely daunting task to express my feelings and appreciation of Belisha in words. I think she was an embodiment of what a good person would aspire to be. I had known Belisha and her family for about 4 years, but it feels like I had known her for ages. Abe and Belisha hosted me when I moved to the area although we had no prior acquaintance. They made me feel at home the moment I met them. I was astonished by their warm welcome and care. Since that time my family had the privilege of calling Belisha and her family as our friends.
Belisha was our go to person to discuss about child rearing, spiritual life, volunteer work, and vision for improvement. Talking to Belisha about any topic, including jokes, would lighten up your day. She was just very special.
Belisha's family has taught me how to live with faith, vision, kindness, charity, and selflessness. They have also showed us how to stay faithful and strong during difficult times.
Although we lost this wonderful woman sooner than we wish, I think would be lucky to accomplish even a portion of what she has achieved in her life. Through Belisha's Foundation, I am very hopeful that her good deeds and legacy will continue.
May God Rest her Soul in Peace, Amen!
Eden Tamirat
from
Addis Ababa
wrote on November 4, 2023
at
7:14 pm
መልካም ስም እና ምግባር አይሞትምም አብሮ አይቀበርምም ግና ከትውልድ ወደ ትውልድ በመልካም አረአያነት ይተላለፋል ። በልሻ ምንኛ የታደለች ሰው ናት ግን? ሞትማ የተራ ጉዳይ እንጂ የማይቀርልን ሃቅ ነው። አፋቸውን ካልፈቱ ህፃናት እስከ አረጋዊያን መልካምነቷን: ሰው ወዳድነቷን:ለጋስነቷን አለማጋነን ከልባቸው በዕንባ ሲገልፁ ከአገር ቤት እስከ አሜሪካ ማየት ምንኛ ያስደስታልም ያስቀናልም ይሄ ምስክርነት ደሞ ዝም ብሎ አልተገኘም በዚህ አጭር ዘመኗ ኖራው ስላሳየችው ነው ። በልሻ በአካል ብትለይም በስራዋ ህያው ሁና ሁሌ ትዘከራለች ፋውንዴሽኑም የሷን ህልሟን ከግብ እንደሚያደርስ ተስፋ እናረጋለን። እኔ ሳቃት ወደ 17 አመት አከባቢ ይሆነኛል በዛ ዕድሜዋ እንኳን ከመጀመርያውም በጣም አስተዋይ እና ጥበበኛ ለባሏም ዘውድ የሆነች ሚስት እንደነበረች ባጭር ግዜ ካየሁት ምስክር ነኝ። ፈጣሪ ደጋጓችን ካስቀመጠበት ከቀኙ ያኑርሽ ።
Tiruwork Badassa
from
aldie
wrote on November 4, 2023
at
1:08 pm
እኔ ነበርኩ ሞኝዋ በፍጹም ያልቅብኩ
ሞትሽን ላልሰማ ጆሮዬን የደፈንኩ
ብርታትሽን ሳየው ተስፋ ማድረግ መረጥኩ
ይዄ ማ በፍጽም አይሆንም እያልኩ
ከ አምላኬ ጋር ክርክር የገጥምኩ
የማተርፍ መስሎኝ ለአባቶች እየነገርኩ
በየደብሩ ዙሬ በስምሽ ያስጸለይኩ
ጨካኙ እንደመጣ እኔ መች አወቅኩ
ብለሽ እኮ ነበር ጌታ አይሳሳት
የፈቀደው ሊሆን ለሴኮንድ አያልፍበት
መረጥሽ ውይ በልሻ ያቺን ቀንና ሰዓት።
ለእኔ ባይፈቅድ አምላክ ባልበቃ ለሽኝት
በሰልስቱ መጣሁ ተገኝሁኝ ከቤት
ፎቶሽ በአግርሞት እያየኝ በትዝብት
የሚለኝ መስለኝ አይ ያገር ልጅ ጎረቤት
ለአንድ ቀን ያልሆንሽ ለመጨረሻ ሽኝት
ሊያብሰለስለኝ ብሎ በሃዘን በቁጭት
ጨዋታ አዋቂ ፍልቅልቅ ያልሽ እህት
ያለሽን አካፍይ ለሌላው ማጋራት
የወንጌሉንም ቃል የኖርሽው በትጋት
ፍጽም አይረሳም በልሻ ያንቺማ ደግነት
ልናገር በጥቂት የሰማሁትን
ሃገር ቤት ሂጄ ያጫወቱኝን
እናሽ “ቦቡሻ” ደግኮ ነበረች ብለው ሲጀምሩ
ተስፋ የሆንሻቸዉ በቦታው ነበሩ
አልብሰሽ አጉርሰሽ የምታስተምሪያቼው
አልሸሸጉም ፍጹም የረዳሻቼው
ይመሰክሩ ነበር እንባ እያነቃቸው
እናቶችም አሉ ደጉመሽ ያስታመምሽያቸው
አለኝታ መመኪያ መኩሪያ የሆንሻቸው
ያንችን እረፍት ዜና ማመን ያቃታቸው
የጨርቆስ ነዋር ልጅ አዋቂ ያለቀሰው
ሞት አዲስ ሳይሆን በመልካምነሽ ነው
አንቺ የመርሶ ፈርት ጭዋታ አዋቂ
በቀልድ እያዋዛሽ ስብስብ አድማቂ
ተረባሽ ወግሽ ሁሉም ትናፍቂ
በቁምነገርሽም ሃዘንን አባራሪ ደስታን ፈንጣቂ
የእኔ እ፟ማ፟_መላ ጠንካራዋ እህት
ለሰፈር ተምሳሌት የልጆቻችን እናት
ሁሌም ትወሽያለሽ በመርሶ ህብርት
በልሻ እህቴ እንውያይ እስቲ ስለ ልጆቻችን
በባእድ ሃገር ላይ ስለምያስጨንቀን
ስለሚቋጠረው ምግብ ቁርስና ምሳቸው
ይዘው ይሚሄዱት መክሰስ መቆያቸው
ርዕሳችንም ነበር ስለ እድገታቸው
በትምህርት በአስተሳስብ ስለመብሰላቸው
በዘመናዊው ትምህርት ስለመዝለቃቸው
ትይኮ ነበር ፈርሃ እግዚአብሄር እንድያድርባቸው
ዘመናዊነት ወግ ባህላቸውን እንዳያስክዳቸው
የሃይማኖቱን ትምህርት ኢትዮጵያዊነቱን መማር አለባቸው
ደግሞ በመሃል ይመጣል ቀልድና ጨዋታሽ
ቁምነገሩን ሁሉ አዋዝትሽ ተንትነሽ
ጭንቀትን አጥፍ ነሽ አስቀሽ አዝናንትሽ
ኧረ ስንቱን ላንሳው በልሻ የአንችን
ሁሌም ትገኝያለሽ በመሀከላችን
አይታሰር እጅሽ መስጠት የለመደው
የፈጠነው መልስሽ በቸግር በጉዋዳው
ሳይሰስት በጭራሽ ማጉረስ የለመደው
መለገስ ማልበስ ማስተማር መለያሽነው
ሁሉንም በድርጊት እንዳሳየሽው
ሰው ተሰብስቦ ቤትሽ የደመቀው
ስምሽን በመጥራት ሃዘኑ የጸናው
በመልካሙ ጸባይሽ በስራሽ እኮ ነው
ነብስሽን ደስ እንዳላት አልጠራጠርም
ስብስብ ስላልን ከሩቅም ከቅርብም
እንዲህ የደመቀው የሞቀው ቤትሽ
ፍንትው ብሎ ይውጣ መልካምነትሽ
ከቶ እንዳይረሳ ተቋርጦ ስራሽ
በስምሽ ቆሞ እንድናይ መታሰቢያሽ
አይዘጋ በርሽ መሰብሰቢያ ቤትሽ
ስምሽም ይዘከር በወዳጆችሽ
ለወገን ለዘመድ አለኝታ ነበርሽ
በአብራክሽ ክፋዮች በውድ ልጆችሽ
በሚያስብልሽ በ_አዛኙ ባልሽ
በወርቅ ቀለማት ተጽፏል ስምሽ
በልሻ እህቴ ተተኪ አለሽ
በበጎ ምግባር በመልካምነት
ሰውን አክባረ በጽኑ እምነት
ተጋድለሽ በሰላም አርፈሻል በእውነት
ነፍስሽ ትረፍ በአጸደ ገነት
እመቤቴ ማሪያም የጌታዬ እናት
ከልጅሽ አማልጃት ይህቺን ደግ እህት
ከደጋጎቹ ጎን ነፍሷን እንዲያኖራት።
ከ ጥሩወርቅ (2023)
Selam
from
Aldie
wrote on November 3, 2023
at
7:05 pm
በልሻዬ ስልክ ትደውልልኝና “ሄሎ ሰላሚቲ እገሌ ታሟል፤ ገንዘብ እያሰባሰብኩ ነው። ልፈልጥሽ ነው የደወልኩት” ትለኛለች። በሌላ ጊዜ ደግሞ መልክት ትፅፍልኛለች “እከሊት ለቅሶ ላይ ናት እንድረስ፤ እኔ ይሄን. . ይሄን እሰራለሁ” ትላለች። በልሻዬ ሁሉን ሰብሳቢ እና ለተቸገረ ቀድሞ ደራሽ ነበረች፡፡
በልሻ ጀግና፤ የማትበገር፤ የጀመረችውን ከግብ ሳታደርስ የማታቆም ነበረች ። One time, we had a fitbit group challenge. ሁላችንም ያቅማችንንም ያላቅማችንም ስንደክም እንውልና ውጤቱ ማታ ሲመጣ አንበሳዋ በልሻ የመጀመሪያውን ስፍራ ትይዛለች። በመጨረሻም ወንዱንም ሴቱንም በልጣ ዋንጫውን ወሰደች።
ልዑልን ስለ በልሻ ጠየኩት “በጣም ብዙ ነው... ካላሃሪ የሄድን ጊዜ ሁላችንንም ፑል መጫወት አስተማረችን። I love playing Pool because of Belisha” አለኝ።
በልሻዬ የጨዋታ ንግስት አድማቂ ነበረች ። “I always remember her laugh…” አለችኝ ሊድያ። ያሬዶም ስለበልሻ “በልሻዬ በጣም የምትመቸኝ፤ የምትቀለኝ፤ ጨዋታዋ ጥርስ የማያስከድን፤ ለቁምነገር ደግሞ ቆምጫጫ ወደኋላ የማትል፤ ትሁት እህቴ ነበረች ። እንደው ከዚህ ሁሉ ሰው እሷ ትሂድ? ... በጣም ከባድ ሃዘን ነው”
በልሻዬ እንግዳ ተቀባይ፤ ሁልጊዜም ጋባዥ ነበረች ። በጣም የሚገርመኝ የማዕድ ቤቷ ጠረጴዛ ላይ ሁልጊዜም ምግብ በሚያምሩ መሶብ ክዳኖች ተደርድሮ ይቀመጣል። ሁልጊዜም የሚበላበት የበልሻ እና የአቤ ቤት ....
በልሻዬ በመንፈሳዊ ህይወቷ ጠንካራ፤ ለልጆቿ አስተማሪ፤ ጠንካራ ሰራተኛ፤ በማህበራዊ ህይወት ቀድሞ ደራሽ፤ መልካምና የልብ ጓደኛ ነበረች ።
በልሻዬ ውዷ እህቴ፤ መልካምነትሽ፤ ቀልድሽ፤ ቁም ነገርሽ ሁልጊዜም ከኛ ጋር ይኖራል። እንወድሻለን፤ እንናፍቅሻለን። ወዳንቺ እስክንመጣ ድረስ ነፍስሽን በገነት ያኑርልን። አሜን።
Jony Girma
from
Addis Ababa
wrote on November 3, 2023
at
5:46 pm
በልሻ በእኔ ዘንድ ያላትን የታላቅነት ቦታ ቀን ተሰጥቶኝ ስተርካት ብውል ደክሞኝ ላቆም እችላለሁ እንጂ እንደማልጨርስ አውቃለው። ለዚህ ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት የቱን አንስቼ የቱን እንደምተወው ግራ ግብት አለኝ።
ስለትውውቃችን በትዝታ ላስታውስ ወይስ ስለ ፀባይዋ ላውሳ? ስለ ተጫዋችነቷ ጨዋታዎቿን እያጫወትኳችሁ ልናገር ወይስ ከልብ ሰው አክባሪ መሆኗን ልመስክር? ስለ ጉብዝናዋ የማውቀውን ልንገራችሁ ወይስ ስለ ትዳርና ቤቷን አክባሪነቷ ልናገርላት? እግዚአብሔርን እንዴት ትፈራው እንደነበር ስለ እምነት ጥንካሬዋ ላውሳ ወይስ ስለ በጎ አሳቢነቷ ልመስክርላት? ስለ እንግዳ ተቀባይነቷ የተቀበለችኝን አቀባበል እያከታተልኩ ልጻፍ ወይስ ስለማይጎድል እህትነቷ? እያንዳንዱ ነገሯ ገጽ በገጽ የሚተረክ ታላላቅ ርዕስ ሆኑብኝ።
ሰው ስለ በልሻ ሲናገር ወይም ሲጽፍ አሊያም ሲያስብ መቼም በኅሊናው ትውስታ ከነ በጎነቷ እየተመላለሰች አሁን የሆነ ያክል እስኪመስለው ደስ የሚያሰኝ በብርሃናት ቀለም የተቅለመለመ ምስል ይታየዋል። አሁን ይህን እየጻፍኩ ሳቋ ፣ ጨዋታዋ ፣ ሰው አክባሪነቷ ፣ እንስፍስፍ የሚለው የእናት አንጀቷ (አሜሪካ ከቤቷ ስትሸኘን ምግብ በምሳ ዕቃ ቁጥር ታደርግና ሳናያት መኪናችን ውስጥ ድብቅ አድርጋ የምታስቀምጥልን) ብቻ የትዝታ ፈረስ ወደኋላ ሽምጥ ወስዶ ብዙ አስታወሰኝ። በተጠየቀው አጭር ጥያቄ የማያጥር መልስ እንደመመለስ አስጨናቂ ነገር የለም።
ለእኔ በልሻን እንደማወቅ ዕድለኝነት የለም። እርሷ ለሁላችን እርሷ ናት። አሁን ግን ወደ ሚሻለው የእግዚአብሔር መንግስት ሄዳለች። እርሱ እግዚአብሔር ነውና የወደደውን አድርጓል። ስለዚህም እግዚአብሔር ይመስገን እያልኩ ሁላችንም ውለታዋን የምንመልሰው ራዕዩዋን በማስፈፀም በመሆኑ በታሰበው በጎ ነገር ሁሉ እንዳንጎድል የአደራ መልዕክቴን አስተላልፋለው።
እግዚአብሔር የአስካለ ጊዮርጊስን ነፍስ በአጸደ ገነት በቅዱሳኑ እቅፍ ያሳርፍልን!
ወንድምሽ ጆኒ ግርማ
Tadesse Kebede
from
Aldie
wrote on November 3, 2023
at
3:19 pm
በልሻን ለመጀመርያ ግዜ የማውቃት ለማስተርስ ድግሪ አብረን በተማርንበት አይዋ ስቴት ውስጥ በሚገኝ አንድ ኮለጄ ነው። ሁላችሁም እንደምታውቋት ፈገግታዋ ፤ ከፊቷ የሚታየው ደስታ እንኳን ሰውን ድንጋይንም ፈገግ ያሰኛል። ትኒሽ ግዜ ከርሷ ጋር ካሳለፉ ደግሞ ቀልዶቿን፣ ልከኛ (appropriate) ፉገራዎችን ማጣጣም የግድ ይሆናል። አሁንምኮ ቢሆነ መሰረቷ “ጨርቆሴ” ስለሆነ “አንተ ዋ! አትፎግር ጎንህን እንዳትወጋÍ” እያለችኝ ይሆናል።
የአይዋ ትምህርቴን ጨርሼ ስወጣ በ 2009 እ.አ.አ. የመጀርያው ወይ ላር የአገሪቱ ኢኮኖሚ በቁልቁለት ጉዞ ላይ ላይ ስለ ነበር እንኳን ከኮለጅ ወጥቶ ስራ መፈለግ፤ ከዶርምም መውጣት አስፈሪ ነበር። ታዲያ በዚህ ስራ ማግኘትና ማጣት ብቻ ሳይሆን አገሪቱ በሙሉ በስራ አጥረት ከመወረሩ የተነሳ ተቀባይ/አሳራፊ ያማይገኝበት ካባድ ግዜ ነበር። ታድያ ብዚህ ግዜ ነው ሌላው የበልሻን አስደናቂ ተግባር ያየሁት። ከቀሯት ጥቂት ገንዘብ ለኢንተርቪው የሚሆኑኝን ሸሚዞች ገዝታ ስርፕራይዝ አረገችኝ (ድንገቴ ፈንጠዝያ!)። ደስታዬ ስራን የሰጠችኝ ያህል ነበር።
ከዚያ በኀላ አቤና ቤልሻ አብረውን በቅርብ እዚህ ቨርጂኒያ መኖር ከጀመሩ በኃላ፤ ሁለቱም ዘወትር ለኔና ለበተሰቤ አሳቢ፣ የትዳር አማካሪ፣ የሒሳብ አያያዝ መምህር፣ የልጅ አስተዳደግ መምህር ... አረ ምኑ ከአቤና ከበሌ ያልተማርነው ምን አለ! እንዴትስ ሁሉን መዘርዘር ይቻላል፡፡
በልሻ ባአካል ከኛጋር ባለመሆና ብንናፍቃትም በመልካም ስራዎቻ እንረካለን፤ በድንቅ ትዝታዎሻ ደስ ይለናል፤ በብልህና በአስተዋይ ልጆቿ እንጸናናለን፡፡
በፍቅራቸው፣ በሰላማችው፣ በመልካም ስራቸው የሚታወሱ ሰዎች ንዑዳን ናቸው። ጠቢቡ ሰሎሞን እንዳለው “መልካም ስም ከመልካም ሽቱ ይበልጣል” እና።
የመልካም ሰዎች ትዝታቸው ሃዘንን ሳይሆን ፈገግታን፣ መልካም ስራቸው ለቅሶ ሳይሆን ደስታን ሊሰጠን ይገባል። መልካም ስም አረፍተ ዘመንን ተሻግሮ ከትውልድ ወደ ትውልድ ይሻገራልና።
ብልህ፣ አስተዋይና ጠንካራ ልጆች ስለተወችልን እነሱን ስናይ ከንፈር የምንመጥበት ሳይሆን ስለተሰጠን ስጦታ፣ ስለቀረልን በረከት የምንደሰትበትና እግዚአብሔርን የምናመሰግንበት መሆን አላበት።
በሃዘን ግዜ ምዕራባውያኑ ከሚጠቀሙባቸው አገላለጾች በከፊሉ
• We cherish your memory.
• Your memory is a treasure.
• Your love and memories walk with us every day.
• Your loving memory will never be forgotten.
• Forever in our heart, and always in our mind.
በኛ ማህበረሰብ ዘንድ ብዙ ግዜ ከሀዘናችን ማጽናናት የምንሞክረው ያጣነውን ወዳጅ ካአእምሮአችን በመፋቅ፤ ፈጽሞ ላለማስታወስ በመሞከር አስኪመስል ድረስ፤ ባይኔ ላይ ታየኝ/ታየችኝ፣ የሆነ ነገር እርሷ(ሱ)ን አስታወሰኝ፣ ከዚህ ከዛ አብረን ሄደን ነበር ወዘተ። ብለን በማስታወስ ወደልቅሶና ወደ ሀዘን የምንመለስባቻው አጋጣሚዎች ብዙ ናቸው። ስልሆነም በተቻለ መጠን የሚያስታውሱን ነገሮችን በመደበቅ ገለል በማድረግ እነርሱን በመርሳት ባለማስታወስ ልንጽናና እንሞክራለን።
እውነታው ግን የሚወዱትን ሰው፣ ከአዕምሮ ማውጣት ፈጽሞ ከባድ ስለሆነ። ትዝታቸውን ለሀዘን ፣ ትውስታቸውን ለስብራት፣ ለለቅሶ ከሚሆነን፤ አብረን ስላሳለፍናቸው መልካም ትዝታዎች እግዚአብሔርን የምናመስግንበት። ትዝታዎቹን በፈገግታ፣ ትውስታዎቹን በደስታ ተቀብለን ቀሪውን ዘመናችን የጤና የሰላም እንዲሆንልን ብናደርግ መልካም ነው።
እህታችን በሌ በአካል ካጠገባችን በመለየቷ ብንናፍቃትም በመልካም ስራዎቻ፤ በድንቅ ትዝታዎቻ፣ በተሰጡን ብልህና አስተዋይ ልጆቿ ልንጽናና መንፈሳችን ሊቃና ይገባል።
መናህየ ወመናዝዘ/አጽናኝና አረጋጊ/ መፈስ ቅዱስ ጽናቱን፣ ብርታቱን፣ መረጋጋቱን ያድለን። አሜን።
Mulatu Mebrate Seifu
from
ADDIS ABABA
wrote on November 3, 2023
at
10:54 am
እንቁዋን እህቴን በልሻዬን በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ከተዋወኳት ከሃያ አመት በላይ ሆኗል፡፡ በዩንቨርሲቲ ቆይታዋ በበጎ አድራጎት ክፍል አገልግሎቷ እና ከዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ በሙሉ ጋር በነበራት መልካም ግንኙነት ትታወቃለች፡፡ ሳቋ እና ጫወታዋ አይጠገብም፡፡ በትምህርቷ፣ በመንፈሳዊ ህይወቷ እና በማህበራዊ ግንኙነቷ የተዋጣላት ሰው ነበረች፡፡ ወደ ሥራ ዓለም ስትቀላቀልም ያላትን ብርታት አጠናክራ ቀጥላለች፡፡ የእግዚአብሔር ፈቃድ ሆኖ ከወንድሜ አቤ ጋር የትዳር አጋር በመሆን ያለን ትስስር ወደ ቤተሰብነት ተሸጋገረ፡፡ በልሻዬ ለቤተሰባችን ሰብሳቢ፣ አሳቢ እና ደስታን ፈጣሪ በመሆን ቆይታለች፡፡ በተለይ ለባለቤቷ ለወንድሜ አቤ ህልሞች ስኬት ቁልፍ ሚና ተጫውታለች፡፡ ለብርቅዬ ልጆቻቻው፤ ለቤቲ፣ ኤሚ እና ሜሉም የሚሳሱላት ልዩ እናት ነበረች፡፡ በልሻዬ በባህሪዋ በጎ፣ መልካም፣ ሩህሩህ፣ ደግ፣ ቅን አሳቢ፣ በፍጥነት ከሰው ጋር የምትግባባ፣ጫወታ አዋቂ እና ደስተኛ ነበረች፡፡ በጣም የሚገርመው ነገር በልሻዬን ከልጅነት እድሜዋ አንስቶ በህይወት እስከ ተለየችን ጊዜ ድረስ የሚያውቃት ሰው ሁሉ የሚገልጻት በአንድ አይነት ሁኔታ ነው፡፡ የማይቀያየር እና የማይዋዥቅ ባህርይ እና ማንነት፤ ምን አይነት መታደል ነው? “ደግ ሰው አይበረክትም” እንደሚባለው ሆነና በረጅሙ ስናቅድ በልሻዬ በአጭሩ ተለየችን፡፡ እኛም መሪር ልቅሶ እና ሀዘን ውስጥ ብንወድቅም የጌታ ፈቃድ ይሁን ብልን ዝም ብለናል፡፡ በልሻዬ ለጥቂት እድሜ የኖረች ቢሆንም የባከነ ጊዜ ያልነበራት በመሆኑ ረጅም አመት ከሚኖሩት በላይ በሁሉም ረገድ ተሳክቶላታል፡፡ አሁን ደግሞ በህልፈቷ ለሌላ ታላቅ አላማ እያሰባሰበችን ነው፤ ለተቸገሩት ድጋፍ የሚያደርግ እና በስሟ The Belisha Foundation ተብሎ የተሰየመው ድርጅት በበጎ አድራጎት ሥራ ለመሰማራት ዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡ እንግዲህ ሁላችንም ለዚህ ድርጅት የበኩላችንን ድጋፍ በማድረግ በልሻ የምትታወቅበትን በጎነትን እና መልካምነትን እናስፋፋ ስሟንም ከመቃብር በላይ እናውለው፡፡
እግዚአብሔር አምላክ የአስካለ ጊዮርጊስን ነፍስ በአጸደ ገነት በቅዱሳኑ እቅፍ ያሳርፍልን!
ዲያቆን አሳምነው ዳዲ
from
አዲስ አበባ
wrote on November 3, 2023
at
10:20 am
“ከመልካም ሽቱ መልካም ስም፥ ከመወለድ ቀንም የሞት ቀን ይሻላል።” መክብብ 7፥1
አንዳንዴ የምታውቁት መንፈሳዊ ቃል በመተርጉማን ሲፍታታና ሲብራራላችሁ ''አሃ'' ትላላችሁ አአአ? ከዚያ ባለፈ ቃሉን ያለ ቃል ማውጣት በህይወታቸው የሚተረጉሙ ሰዎችን የማወቅ ዕድል ሲገጥማችሁ ደግሞ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ውሎ አዳሩን አድርጎ ለሚፈልገው ሃሳብ ገላጭ ቃል እንደማይቸግረው የቃለ እግዚአብሔር ጎበዝ የጠቢቡ ሰሎሞንን ቃል ለሃሳቡ ገዝቶ “ጊዜና እድል ግን ሁሉን ይገናኛቸዋል።” መክብብ 9፥11 በማለት የዕድልና ጊዜ ኅብረት ውጤትን በዚህ ታላቅና እውነተኛ ቃል እንደሚገልጽ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ውዬበት ባላድርም በዚያ ሰው መንፈስ ሆኜ እኔም እንዲህ ልበል.....ስለ በልሻ እንዳወራ እንድተርክም ጊዜና ዕድል አገናኙኝ።
በልቤ የማከብረው ወዳጄ ከዕለታት በአንዱ (ጠቢቡ ሰለሞን ''ጊዜ'' ብሎ ባመለከተው) ቀን ላይ ወደ አረፋፋዱ ደወለልኝና ለቅሶ ገጥሞኝ ወደ አሜሪካ ልሄድ ነው ሲለኝ ያለሁበትን ኑሮ አስታውሼ እኛ አልቅሰን ያልተሳካልንን ለለቅሶ አሜሪካ ትለኛለህ እንዴ ብዬ ትክክልን ስቼ ስህተትን አልሳትኩ። ያለ ማቋረጥ በደ አምሳ ደቂቃ በማያንስ መልኩ የማያጥረውን ደግነት እጅግ በማሳጠር ስለ አንዲት ሴት ነገረኝ። ባልጨረሰው እያልኩ ቆይ አንዴ መልሼ ልደውል አለኝ። ምን እንደገጠመው ባላውቅም በዝምታ ስልኩን ዘጋሁት....መልሶ ሲደውል አንድ ጥያቄ ብቻ ጠየኩት....ከነገርከኝ ታሪክ አንጻር እኔ ለምን ተፈለኩኝ? እሱም ሁለት ምላሽ ሰጠኝ
አስቀድሜ የወይዘሮ በለጠች ሞላ (በልሻዬ) የአርባ ቀን መታሰቢያ በተስፋ አዲስ ካንሰር ህሙማን ማዕከል እንዳዘጋጅና እንንዳስተባብር ቀጥሎም የእርሷን ህይወት በአጭር ዘጋቢ ፊልም እንድሠራ......ቀጭን ግን ከባድ ትዕዛዝ...
የአርባ ቀኑ እንኳን ብዙም አይቸግረኝም። በብዙ ልምድ ያካበትኩት ችሎታ አለኝ ብዬ ተንቀባረርኩ። ነገር ግን አልኩት ለጆኒ ላንተ ባሳየችህ ጥቂት በጎነቷ እንኳ ያለማቋረጥ በሰዓታት የምትተርክላትን ሴት ከ20 ደቂቃ ባነሰ ሊያውም የሕይወት ጉዞዋን የሚዳስስ ዘጋቢ ፊልም እንዴት ነው የማዘጋጀው?
....የእርሱ መልስ ደግሞ ጥቅልል ያለ ነበር። ''አላውቅልህም'' ብቻ እኔ የማውቀው በቶሎ ዘጋቢው ፊልም እንደሚፈለግ ነው አለኝ።
አያ ሙሌ ትዝ አለኝ። አያ ሙሌማ ገጣሚ ሙሉጌታ ተስፋዬ ነው። ''ከሚያዝኑ ጋር ማዘን ከቻልክ ስለ ሐዘን ትጽፋለህ ስለ ማዘናቸውም ትገጥማለህ። እንዲሁ ደስ ከሚላቸው ጋር ደስ ካለህ ከእነርሱ በላይ ደስታውን ታብራራለህ'' ብሎ ነበር። በአያ ሙሌ በመጀመሪያው ምሳሌ ተስማምቼ ካዘኑት ይልቁንም በደረሱኝ መረጃዎች ኃዘናቸውን መግለጫ ቃል ከጠበባቸው ጋር ራሴን በማጠጋጋት ነገረ ስለ በልሻ መጻፍ የጀመርኩ። በዚህም ጠቢቡ ዕድል ያለው በእኔ ዘንድ ተፈፀመ። የእድለኛን ሰው ታሪክ መዘገብ ከዕድሉ ተካፍሎ ዕድለኛ መሆን ነው።
ለዝግጅት የሚረዳኝን መረጃዎችን ከአቶ ጆኒ ግርማና ዶክተር ሙላት በበቂ ሁኔታ ላግኝ እንጂ ወደ ጨርቆስ (የትዝታዋ መንደር) ጎራ ብዬ ከሚወዷት ከነ ቤተልሄም ምስጋናው (ከሚዜዎቿ አንዷ በሆነችው) እንዲሁም በውልደ ሰማዕት ሰንበት ትምሕርት ቤት አባላት ፣ በጊዜዋ ከሚያውቋት ጋር ስለ እርሷ አጠያይቄ ነበር። ሁሉም ስለ በጎነቷ ተረኩልኝ። አረ ቀን እንኳ ብርሃንና ጨለማ አለው። እንደው የጨለመችባቸው የሉም? ብላቸው አማርኛቸው ይለያያል እንጂ ሀሳባቸው ሲጨመቅ መልሳቸው ''ጨለማ ከብርሃን ኅብረት የለውም'' የሚል ነው። እንዴት ሁሉንም በብርሃኗ ተዋወቀቻቸው??? እኔ እንጃ።
እኔን ግን ከዕረፍቷ በኋላ ባለ ብርሃናማ በጎ ስሟ ምስክርነት ባለችበት ሆና ተዋውቃኛለች። እኔም ባለችበት እንደሆነች ተዋውቄአታለው።
መጽሐፍ ''ከመልካም ሽቱ መልካም ስም፥ ከመወለድ ቀንም የሞት ቀን ይሻላል።” መክብብ 7፥1 ብሎ የተናገረውን ለእኔና ለሚመስሉኝ እንድንረዳው መተርጉማኑ እንዲህ ብለው ተርጉመውታል .... ''የመልካም ሽቶ በጎ መዓዛ ርቆ እንደሚሸት የመልካም ስም እንዲሁ ርቆ ያውዳል'' ይላሉ። ጠይቁኝ ልመስክርላችሁ። ለምሳሌ የማቀርብላችሁ ግን በልሻን ነው። እንኳን በቁሟ የተዋወቋትን በሞቷ የተዋወቀችንን እኔን መሰሎች የሚማርክ አኗኗር ኖራ ማለፏን በብዙ ምስክሮች ተረጋግጧል።
ለዘጋቢ ፊልሙ አስፈላጊ ዶክመንቶች ተልከውልኝ የሚያውቋትም ተርከውልኝ ስለ እርሷ ስረዳ ወንድሜ ጆኒን ''ለለቅሶ አሜሪካ ድረስ?'' ባልኩት ምፀታዊ ቃል ራሴን ወቅሼ ለእንዲ ያለች አብረቅራቂ ሴት ለሽኝቷ አሜሪካ መሄድ አይደለም ቢቻል ኖሮ ያለን ከፍሎ በሰማይ በሚደረገው አቀባበል ላይም መሳተፍ ያስመኛል። ብዙ የሚነገርላት ሴት መሆኗን ብረዳም ላጠቃለው።
ቤተ ክርስቲያን ለልጆቿ የምትመርቀውን ከኅብረቷም አንዷ ለሆነችው ለበሌ በነጠላ እንዲህ ልመርቃት። የምታውቋት በነገርኳችሁም ያወቃችኋት አሜን በሉልኝ።
አጭር ምኞቴ ለክርስትና እህቴ
በዚህ ምድር እንዳውቅሽ ተመኝቼ ምኞቴ ባይሳካም እንደ ክርስትና እምነት ተከታይነቴ አንቺን በሰማይ እንዲያገናኘኝ ይህን በጻፍኩበት ቀን በፀሎቴ ተመኝቻለው። እግዚአብሔር ሁሉን አድራጊ ነው። ጠይቁኝ ብሏልና ጠይቄዋለው። በዚህም በስሟ በሚቋቋመው በጎ አድራጎት ላይ ለመሳተፍ እንኳን እርሷን ማወቅ ስለ እርሷ ማወቅ በቂ መሆኑን አረጋግጫለው።
ሃሳቤን ሳልዘጋ ከቤተ- ክርስቲያን አንዱ የሆንኩት እኔ ከቤተ ክርስቲያን አንዷ ለሆንሽው በልሻዬ በቤተ ክርስቲያን ቃል እንዲህ እያልኩ ልመርቅሽ....
አንቺ ከክርስቲያን ወገን የሆንሽ ሆይ በክርስቲያን ኅብረት እንዳልጎደልሽ ከቤተ ክርስቲያን እንዳለመጥፋትሽ ክብርት በምትሆን በደብረ ፅዮንና በሰማይ ባለች ነፃ በምታወጣ በኢየሩሳሌም ከሚሰበሰቡት ብዙኃን አንዷ አድርጎ አብሮ ይሰብስብሽ። በሕይወትሽ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ማኅሌት ፣ ውዳሴ ፣ ቅዳሴና ዝማሬ በፍቅር እንደምትሰሚ ከጣዕሙ ብዛት አጥንትን የሚያለመልመውን የመላዕክትን ዝማሬ ያሰማሽ። የእሳት ነበልባል ድንኳኖች ወደ ተተከሉበት የካህናት አለቃ (ኢየሱስ ክርስቶስ) ወዳለበት ያግባሽ። ንፁሕ አክሊሉን ያድርግልሽ። ብሩህ ልብሱንም ያጎናጽፍሽ። የቅዱሳን ማኅበር ወዳለበት ያግባሽ። ያስተማሩ የሐዋርያትም ማኅበር ድል የነሱ የሰማዕታትም ማኅበር (ከሰማዕቱ ቂርቆስ ከቅዱሳኑም ጋር) ብሩካን የሚሆኑ የጻድቃንም ማኅበር የተሾሙ የካህናት ማኅበር ትጉሃን የሚሆኑ የመላዕክትም ማኅበር ፍፁማን ደናግልና የመነኮሳት ማኅበር ወዳለበት ያግባሽ። ከሁሉ በላይ ከሆነች ከአንዲት ቤተ ክርስቲያን ፍፁም አንድነቷ ሁሉ ጋራ ከነርሱም ጋራ ታቦር ዘዶር ወዳለችበት ይህችውም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ባለችበት ነፍስሽን በሰላም ያሳርፈረልን።
በሰላም እረፊ የብዙኆች ሰላም።
ዲያቆን አሳምነው ዳዲ