How did Belisha touch you?

Beletech Molla, Belisha, is a beloved mother, wife, sister, and friend who left tremendous impact on the lives of countless children and community elders who were in need. How did Belisha touch you and your family? How long had you known her?

በልሻ የተወደደች እናት፣ ሚስት፣ እህት፣ እና ጓደኛ ነበረች፡፡ በችግር ላይ ለነበሩ ስፍር ቁጥር ለሌላቸው ልጆች እና አዛውንቶች ህይወት ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ ትታ አልፋልች። በልሻ በናንተም ሆነ ቤተሰቦቻችሁ የምትታወሰው እንዴት ነው? ለምን ያህል ጊዜ ነው ያወቃችሁሃት?

Click on “Write a new entry” below to start writing your entry.
Note: We noticed that using emoji will cause issues submitting your entry. Don’t use emoji in your entry.

Write a new entry for the Guestbook

 
 
 
 
 
 
 
Fields marked with * are required.
Your E-mail address won't be published.
It's possible that your entry will only be visible in the guestbook after we reviewed it.
We reserve the right to edit, delete, or not publish entries.
Tirsit Negash Tirsit Negash from Aldie
November 1, 2023 at 6:54 pm
በልሻዬ የፍቅር የወዳጅነት የለጋስነትና የእንግዳ  ተቀባይነት እንዲሁም የእናትነት ተምሳሌት ነበረች ሰው በልቶ የሚጠግብ የማይምስላት ደግ ; ፈገግታዋ ሁሌ ከፊቷ የማይጠፋ የእኛም የሳቃችን ምንጭ ጨዋታ ከቁም ነገር ጋር የምትችልበት እህታችን ሰብሳቢያችን እና መሪያችን ነበረች
ከብዙ ትዝታዎቼ በቅርቡ የሆነውን ላስታውስ ጠዋት ጠዋት ወክ እናድርግ ብለን ከእህቶቼ ጋር በምንጏዝበት ጊዜ እሷም ልጆች ት/ቤት ስታደርስ ታየናለች እናም ምን እያደረጋችሁ ነው ?ብላ ስትጠይቀን ወክ እንደምናደርግ ነገርናት እሷም በመሳቅ እኔም አብሬያችሁ እሆናለሁ በማለት እንዴት ወክ እንደሚደረግ በማሳየት ጉዞአችንን ጀመርን እኛም ትንሽ እንደሄድን ላብ በላብ ሆንን እንዴ ቀስ በይ እንጂ በልሻዬ ስንላት እናንተ እኮ እንደቁራሌው ነው ሰፈር የምትዞሩት እንጂ ወክ አይባልም ብላ ያሳቀችንንም ያሳቀቀችንንም አልረሳውም ከዛም መልስ በቤቷ ቁርስ አዘጋጅታ በመጋበዝ ድካማችንን ታጠፋልን ነበር :: ስንቱን ልፃፈው በውስጤ ብዙ ነገር አለ ግን እግዚአብሔር እርሱ የወደደውን አደረገ ሁሌም ውስጣችን ነሽ እንወድሻለን በልሻዬ እኛም መጥተን እስከምናገኝሽ በሰላም እረፊልን

አምላከ ቅዱሳን እህታችንን ከደግጎቹ ጋር ይደምርልን
Please wait...